Learn Orthodox Stained Glass Logo
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ
ዲያቆን
ገጽ 1
ግዕዝ

መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት ወይጼልሎ ለዝንቱ መሥዋዕት ወይቄድሶ። በጽሙና ወበፍርሀት ቁሙ ወጸልዩ ከመ ሰላሙ ለእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌየ ወምስለ ኵልክሙ።

አማርኛ

ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት፤ ይህችስ ሰዓት ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት፤ መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት ናት፤ ይህን መሥዋዕቱን የሚሰውርበትና የሚያከብርበት። በጸጥታና በመፍራት ቁሙ፤ የእግዚአብሔር ሰላም ከእኔና ከእናንተ ጋራ ይሆን ዘንድ ጸልዩ።

እንግሊዝኛ

How awful is this day and how marvelous is this hour wherein the Holy Spirit will descend from heaven and overshadow and hallow this sacrifice. In quietness and in fear, stand up and pray that the peace of God be with me and with all of you.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 2
ግዕዝ

ምነ በሐ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት ዓረፋቲሃ በዕንቍ ጳዝዮን፤ እምነ በሐ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

አማርኛ

ሰላም ላንቺ ይሁን፤ እናታችን ቤተ ክርስቲያን፤ ግድግዳዎችሽ በጳዝዮን ዕንቁ የተጌጡ ናቸው፤ ሰላም ላንቺ ይሁን እናታችን ክብርት ቤተ ክርስቲያን

እንግሊዝኛ

Peace be unto you, our mother, O honorable church. Thy walls are embroidered with Topaz. Peace be unto you, our mother, O honorable church.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 3
ግዕዝ

ስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ እምኵሉሰ ፀሐይ አርአየ። መስቀል አብርሃ በከዋክብት ዐሠርገወ ሰማየ።

አማርኛ

መስቀል አበራ! በኮከቦች ሰማይን አስጌጠ። ከሁሉም ፀሐይን አሳየ። መስቀል አበራ! በኮከቦች ሰማይን አስጌጠ።

እንግሊዝኛ

The cross shined and had the heavens embroidered with stars. Of all the sun is seen. The cross shined and had the heavens embroidered with stars.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 4
ግዕዝ

ሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ

አማርኛ

በጎን የሚያደርግ ሰንበትንም የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው። ወደ እግዚአብሔር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ሁሉ ይለይ ይሆን? አይበል በጎ ያደረገ ሰንበትንም የሚያከብር ጻድቅ ነው።

እንግሊዝኛ

Blessed is he who does blessed deeds and honors the Sabbath. Let him not question whether he will be outcast from the multitudes if he was to enter into the worship of God. Blessed is he who does blessed deeds and honors the Sabbath.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 5
ግዕዝ

ሌ ሉያ እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቅዳሴ ወኢሰምዐ በጽሐፍተ ቅዱሳት ወኢተአገሠ እስከ ይፌጽሙ ጸሎተ ቅዳሴ

አማርኛ

ሃሌ ሉያ በቅዳሴ ጊዜ ከምዕመናን ወገን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገሥ ከቁርባን ባይቀበል ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ

እንግሊዝኛ

Halleluia! If there be anyone of the faithful that hath entered the church at the time of mass and hath not heard the holy Scriptures, and hath not waited until they finish the prayer of the Mass, and hath not received the holy communion, let him be driven out of the church:

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 6
ግዕዝ

ኢተወክፈ እምቁርባን ይሰደድ እምቤተ ክርስቲያን እስመ አማሰነ ሕገ እግዚአብሔር ወአስተሐቀረ ቁመተ ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ ከመዝ መሀሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ

አማርኛ

የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ በክርስቶስ ፊት መቆምን አቃሏልና ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ ሲሉ አስተማሩን

እንግሊዝኛ

for he hath violated the law of God and disdained to stand before the heavenly King, the King of Body and Spirit. This the Apostles have taught us in their canons.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 7
ግዕዝ

ንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ውስቴታ መና ኅቡዕ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኵሉ ዓለም

አማርኛ

የተሰወረ መና በውስጧ ያለባት የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ፤ ከሰማያት የወረደ ሕብስት ለሰው ሁሉ ድኅነት የሚሰጥ

እንግሊዝኛ

Thou art the pot of pure gold wherein is hidden the manna, the bread which came down from heaven giving life unto all the world.

በ AI ለመማር ይጫኑ