ጋ ዘእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ ምስለ መንፈስከ።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን ከመንፈስህ ጋር
The grace of God be with you. And with Thy spirit
አኵቶ ለአምላክነ። ርቱዕ ይደሉ። አጽንዑ ሕሊና ልብክሙ።
ፈጣሪያችንን እናመስግን፤ እውነት ነው ይገባል፤ የልባችሁን አሳብ አጽኑ።
Let us glory our God. It is right, it is just. Strengthen the thought of your heart.
ነ ኀበ እግዚአብሔር አቡነ ዘበሰማያት አቡነ ዘበሰማያት አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
ከእግዚአብሔር ዘንድ አለን፤ አባታችን ሆይ አባታችን ሆይ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
We lift them unto the Lord our God. Our Father who art in heaven, Our Father who art in heaven, Our Father who art in heaven, lead us not into temptation.
ህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚአብሔር አብ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ ኪዳነ ንሴብሐከ እግዚኦ
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚአብሔር አብ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ አቤቱ እናመሰግንሃለን
The priest will read the "O God the Father..." Prayer of the Covenant. Oh, we thank you Thee
ህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ ኪዳነ ንዌድሰከ እግዚኦ
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ አቤቱ አንተን እናመሰግናለን
The priest will read the "O Lord, Jesus Christ" Prayer of the Covenant. Oh Lord, we praise Thee
ህኑ የኪዳን ጸሎት “ንዌልሰከ ለከ ዘንተ ቅዱሰ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ አሜን
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “ንዌልሰከ ለከ ዘንተ ቅዱሰ…” የሚለውን በንባብ ያሰማሉ፤ አሜን
The priest will read " Thrice over ..." prayer of the covenant. Amen
ቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ . . . በሰላመ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሆይ . . .
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር . . . እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ . . .
Our Father in Haven . . . Hail Mary . . .
ሥሉስ ቅዱስ መሐለነ ኦ ሥሉስ ቅዱስ መሐከነ ኦ ሥሉስ ቅዱስ ተሣሃለነ፤ ተፈሥሒ ተፈሥሒ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ድንግል ምልዕተ ጸጋ
ልዩ ሦስትነት ሆይ ማረን ልዩ ሦስትነት ሆይ ራራለን ልዩ ሦስትነት ሆይ ይቅር በለን፤ ጸጋን የተመላሽ ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ
O! Holy Trinity, Pity us, O! Holy Trinity, Spare us, O! Holy Trinity, have mercy upon us. Rejoice rejoice rejoice, O! Virgin Mary, full of grace
ግዚአብሔር ምስሌኪ። ተንብዪ ወስእሊ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጢአተነ።
እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ወደ ተወደደ ልጅሽ ከምስኪን አማላጅነቱ፤ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ።
The Lord is with Thee. Intercede and pray to Thy beloved Son: That He may forgive us our sins.
ብሐት ወክብር ለሥላሴ ቅዱስ ይደሉ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በኵሉ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን
Glory and honor are meet to the Holy Trinity, the Father, the Son and the Holy Spirit at all times. Both now and ever and world without end. Amen.
ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነ ዘትቤሎሙ ለአርዳኢከ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲከ ንጹሐን እስመ ብዙኃን ነቢያት ወጻድቃን ፈተዉ ይርአዩ ዘአንትሙ ትሬእዩ ወኢርእዩ ወፈተዉ ይስምዑ ዘአንትሙ ትሰምዑ ወኢሰምዑ ወለክሙሰ ብፁዓት አዕይንትክሙ እለ ርእያ ወእዝንክሙ እለ ሰምዓ ወአምሰለነኒ ረሥየነ ድልዋነ ለሰሚዕ ወለገቢረ ቃለ ወንጌልከ ቅዱስ በጸሎተ ቅዱሳንከ።
ለተቀደሱ ደቀ መዛሙርትህና ለንጹሐን ሐዋርያትህ እንዲህ ያልካቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም፤ እናንተ ግን ያዩ ዓይኖቻችሁ የሰሙ ጆሮቻችሁም ብፁዓን ናቸው፤ እኛንም የቅዱሳኑን ጸሎት ሰምተህ የወንጌልህን ቃል ለመስማትና ለመሥራት የበቃን አድርገን።
O Lord Jesus Christ, our God, who didst say to Thy holy disciples and Thy pure apostles: Many prophets and righteous men have desired to see the things which Ye see and have not seen them, and have desired to hear the things which Ye hear and have not heard them, but You, blessed are Your eyes that have seen and you ears that have heard, Do Thou make us also like them meet to hear and to do the word of Thy Holy Gospel through the prayer of the saints.
ልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ። ይረስየነ ድልዋነ ለሰሚዐ ወንጌል ቅዱስ።
ክቡር ስለሚሆን ስለ ወንጌል ጸልዩ፤ ወንጌሉን ለመስማት የበቃን ያድርገን
Pray for the Holy Gospel. May He make us meet to hear the Holy Gospel.
ዝከር ካዕበ እግዚኦ እለ አዘዙነ ከመ ንዝክሮሙ በጊዜ ጸሎትነ ወስእለትነ ዘንገብር ኀቤከ። ኦ እግዚእነ አምላክነ እለ አዕረፉ እምቅድሜነ አዕርፎሙ ወእለኒ ድውያን ፈውሶሙ ፍጡነ እስመ አንተ ውእቱ ሕይወተ ኵልነ ወተስፋ ኵልነ ወመድኃኒተ ኵልነ ወአንሥኦተ ኵልነ ወለከ ንፌኑ አኰቴተ ውስተ ልዕልና ሰማያት ለዓለመ ዓለም።
ዳግመኛም አቤቱ በጸሎታችንና በልመናችን ጊዜ እናስባቸው ዘንድ ያዘዙንን አስባቸው። አምላካችን ሆይ፤ ከእኛ አስቀድመው ያረፉትን አሳርፋቸው፣ የታመሙትንም ፈጥነህ ፈውሳቸው፤ አንተ የሁላችን ሕይወት፣ የሁላችን ተስፋ፣ የሁላችን አዳኝና የሁላችን አስነሺ ነህና፤ ለአንተም ወደ ሰማየ ሰማያት ምስጋናን እንልካለን ለዘላለሙ አሜን።
Remember again, Lord them that have bidden us to remember them at the time of our prayers and supplications wherewith we make request of Thee. O Lord our God, give rest to them that have fallen asleep before us, heal speedily them that are sick, for Thou art the life of us all, the hope of us all, the deliverer of us all and the raiser of us all, and to Thee we lift up thanksgiving unto the highest heaven, world without end.
ዕለቱን ምስባክ ሕዝቡ ከዲያቆኑ ጋር እየተቀበሉ በዜማ ያሰማሉ
የዕለቱን ምስባክ ሕዝቡ ከዲያቆኑ ጋር እየተቀበሉ በዜማ ያሰማሉ
The Deacon shall sing from the Psalms a text which suits the day
ክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ ወኢይፈርህ እምነገር እኩይ ፕዑስ ልቡ ለተወክሎ በእግዚአብሔር። መዝ. ፻፲፩፥፯
የጻድቃን መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል፤ ክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው። መዝ. ፻፲፩፥፯
The righteous shall be in everlasting remembrance; he shall not be afraid of evil tidings. His heart is established, trusting in the Lord. (Psalm 111:7)
ሌ ሉያ ቁሙ ወአጽምዑ ወንጌለ ቅዱሳ ዜናሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሃሌ ሉያ! ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቅዱስ ወንጌል ቆማችሁ ስሙ
Halleluia, stand up and hearken to the Holy Gospel, the message of our Lord and Savior Jesus Christ.
ግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
The Lord be with you all. And with Thy spirit
ንጌል ቅዱስ ዘዜነወ ማቴዎስ/ማርቆስ/ሉቃስ (ዘሰበከ ዮሐንስ) ቃለ ወልደ እግዚአብሔር
(ማቴዎስ/ማርቆስ/ሉቃስ/ዮሐንስ) የተናገረው/የሰበከው የእግዚአብሔር ልጅ ቃል የሚሆን ቅዱስ ወንጌል
The holy gospel which Matthew/Mark/Luke/John preached the Word of the Son of God.
ብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላክየ ኵሎ ጊዜ።
ጌታዬና አምላኬ ክርስቶስ ሆይ፤ ሁል ጊዜ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል።
Glory be to Thee, Christ my Lord and my God, at all times.
ፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረዳአነ ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ መዝሙረ ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ
በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ያዕቆብንም አምላክ አመስግኑ፤ መዝሙሩን ያዙ ከበሮውንም ስጡ፤ በበገናና በክራር የተስማማ ነው።
Sing aloud unto God our strength: make a joyful noise unto the God of Jacob. Take a psalm, and bring hither the timbrel, the pleasant harp with the psaltery.
ወንጌለ መራሕከነ ወበነቢያት ናዘዝከነ ዘከዚከ አቅረብከነ ስብሐት ለከ
በጾም ጊዜ “በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ” በሚለው ፈንታ የሚባል፦ በወንጌል መራኸን፤ በነቢያትም አጽናናኸን፤ ካንተም አቀረብኸን፤ ክብር ምስጋና ይገባሃል።
During the fast the following will be said instead of the "Sing aloud": Thou hast guided us with the Gospel, comforted us with the prophets, and drawn us nigh unto thee. Glory be to Thee
ማቴዎስ ወንጌል ይነበባል
የማቴዎስ ወንጌል ይነበባል
Reading the Gospel According to Matthew
ማርቆስ ወንጌል ይነበባል
የማርቆስ ወንጌል ይነበባል
Reading the Gospel According to Mark
ሉቃስ ወንጌል ይነበባል
የሉቃስ ወንጌል ይነበባል
Reading the Gospel According to Luke
ዮሐንስ ወንጌል ይነበባል
የዮሐንስ ወንጌል ይነበባል
Reading the Gospel According to John
አምን አበ ዘበአማን ወነአምን ወልደ ዘበአማን ወነአምን መንፈሰ ቅዱሰ ዘበአማን ህልወ ሥላሴሆሙ ነአምን
በእውነት አብን እናምናለን በእውነት ወልድንም እናምናለን በእውነት መንፈስ ቅዱስንም እናምናለን፤ የማይለወጥ ሦስትነታቸውን እናምናለን።
We believe in the very Father, We believe in the very Son, and we believe in the very Holy Spirit, we believe in their unchangeable Trinity.
ሉ ኪሩቤል ወሱራፌል ያዐርጉ ሎቱ ስብሐተ እንዘ ይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እነዚያ ኪሩቤልና ሱራፌል ምስጋናን ያቀርቡለታል፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ነህ እያሉ።
Those cherubim and seraphim offer to Him glory saying; Holy Holy Holy art thou God, Father, Son and the Holy Spirit.
ኑ ይመስለከ እምነ አማልክት እግዚኦ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኃይለከ ወአድኃንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ።
አቤቱ ከአማልክት ወገን የሚመስልህ ማነው ተአምራትን የምታደርግ አንተ ነህ፤ ኃይልህን ለወገኖችህ አሳየሃቸው፤ በክንድህም ወገኖችህን አዳንካቸው።
Who is like unto thee, O lord, among the gods? Thou art the God that doest wonders: thou hast declared thy strength among the people. Thou hast with Thine arm redeemed Thy people.
ርከ ውስተ ሲኦል ወአዕረገ ፃዋ እምህየ ወጸገወነ ካዕበ ይእዜኒ ከመ እንኩን ፍቱሐነ እስመ መጻእከ ወአድኃንከነ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል ቡሩክ አንተ እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኃንከነ።
ወደ ሲኦል ወርደህ ምርኮን ከዚያ አወጣህ፤ ዳግመኛም ነጻነትን ሰጠኸን፤ መጥተህ አድነኸናልና፤ ስለዚህ ነገር እናመሰግንሃለን፤ አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቸር ነህ እንልሃለን፤ መጥተህ አድነኸናልና።
Thou didst go into Kades and the Captives rose up from there, and thou didst grant us again to be set free, for thou didst come and save us. For this cause we glorify thee and cry unto thee saying, Blessed art thou, Lord Jesus Christ, for thou didst come and save us.
ዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ ወርኢነ ስብሐቲሁ ከመ ስብሐተ ፩ዱ ዋሕድ ለአቡሁ ቃለ አብ ሕያው ወቃለ ማሕየዊ ቃለ እግዚአብሔር ተንሥአ ወሥጋሁኒ ኢማሰነ።
ቃል በመጀመሪያ ነበር፤ ይህ ቃል የእግዚአብሔር አብ ቃል ነው፤ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በባሕርያችንም አደረ፤ ከአባቱ እንደተወለደ እንደ አንድ ልጅ ክብር የሚሆን ክብሩን አየን፤ የሕያው አብ ቃል የሕይወት ቃል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ተነሣ፤ ሥጋውም አልፈረሰም።
In the beginning was the Word, the Word was the Word of God: The Word was made flesh, and dwelt among us, and we he held his glory, the glory as of the only-begotten of the Father, the Word of the living Father, and the life-giving Word, the Word of God, rose again and his flesh was not corrupted.
ኡ ንኡሰ ክርስቲያን። ተንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
የክርስቲያን ታናሾች የሆናችሁ ውጡ፤ ለጸሎት ተነሡ፤ አቤቱ ይቅር በለን
Go forth, Ye catechumens. Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
ልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር
ሐዋርያት ለሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ለቀናች ክብር ስለምትሆን ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ
Pray for the peace of the one holy apostolic church orthodox in the Lord.
ርያላይሶን። ተንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ኪርያላይሶን። ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Kyrie eleison. Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
ልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ ውስቴታ፤ ሕዝብ፦ ማኅበረነ ባርክ ዕቀብ በሰላም፤ ዲያቆን፦ ንበል ኵልነ በጥበበ እግዚአብሔር ጸሎተ ሃይማኖት
ስለዚች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በውስጧ ስላለን ስለ አንድነታችን ጸልዩ፤ ሕዝብ፦ አንድነታችንን ባርክ በሰላም ጠብቅ፤ ዲያቆን፦ በእግዚአብሔር ጥበብ ሁላችንም የሃይማኖት ጸሎት እንበል
Pray for this holy church and our congregation. Congregation: Bless and keep us in peace. Deacon: Let us say the Creed in the wisdom of God.
አምን በ፩ዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ሁሉን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን
We believe in one God
አምን በ፩ዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ሁሉን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን፤
We Believe in one God the Father almighty, maker of heaven, earth and all things visible and invisible.
ነአምን በ፩ዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋሕድ ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም፤ ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ አማናዊ ዘተወልደ ወአልቦ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በሕላዌሁ።
ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል፤
And we believe in one Lord Jesus Christ, the only-begotten Son of the Father who was with Him before the creation of the world: Light from light, true God from true God, begotten not made, of one essence with the Father:
በእንቲአሁ ኵሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ ዘበእንቲአነ ለእጓለ እመሕያው ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት ወተሠገወ እምመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል ወኮነ ሰብአ።
ሁሉ በእርሱ የሆነ፣ በሰማይም በምድርም ካለው ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎቹ እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፤
By whom all things were made, and without Him was not anything in heaven or earth made: Who for us men and for our salivation came down from heaven, was made man and was incarnate from the Holy Spirit and from the holy Virgin Mary.
ተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ።
ሰው ሆኖ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ፤ መከራን ተቀበለ፤ ሞተ፤ ተቀበረም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ፤ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ አረገ፤ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ፤
Became man, was crucified for our sakes in the days of Pontius Pilate, suffered, died, was buried and rose from the dead on the third day as was written in the holy scriptures: Ascended in glory into heaven, sat at the right hand of His Father,
ግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማሕየዊ ዘሠረፀ እምአብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት።
ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሰረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው፤
and will come again in glory to judge the living and the dead; there is no end of His reign. And we believe in the Holy Spirit, the life giving God, who proceedeth from the Father; we worship and glorify Him with the Father and the Son; who spoke by the prophets;
ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለስርየተ ኃጢአት ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም አሜን።
ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፤ ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፤ የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።
And we believe in one holy, universal, apostolic church; And we believe in one baptism for the remission of sins, and wait for the resurrection from the dead and the life to come, world with out end. Amen!
ንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም አሜን።
የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።
And wait for the resurrection from the dead and the life to come, world with out end. Amen!
ከመ አንጻሕኩ እደውየ እምርኩስ እንዲሁ ንጹሕ አነ እምደመ ኵልክሙ። ለእመ ደፈርክሙ ወቀረብክሙ ውስተ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ ኢይትዋኃሰኒ እምተወክፎትክሙ። ንጹሕ አነ እምጌጋይክሙ ኃጢአትክሙ ላዕለ ርእስክሙ ይገብእ ለእመ ኢቀረብክሙ በንጽሕና።
እጄን ከእድፍ እንደታጠብሁ እንዲሁ ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ፤ ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም፤ ኃጢአታችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጂ በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ።
As I have cleansed my hands from outward pollution, so also I am pure from the blood of you all. If you presumptuously draw nigh to the body and blood of Christ I will not be responsible for your reception thereof. I am pure of your wickedness, but your sin will return upon your head if you do not draw nigh in purity.
መቦ ዘአስተሐቀረ ዝንቱ ቃለ ካህን ወእመቦ ዘሣሐቀ ወእመቦ ዘተናገረ ወእመቦ ዘቆመ በክፋት ውስተ ቤተ ክርስቲያን ይለቡ ወያእምር ከመ ያመረረ ሎቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወያመጽእ ላዕለ ርእሱ መርገመ ወኢበረከተ ወይረክብ እምኀበ እግዚአብሔር እሳተ ገሃነም ወኢስርየተ ኃጢአት።
ይህን የካህኑን ቃል ያቃለለ ወይም የሳቀ ወይም የተናገረ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው በእርሱም እንደተናደደ ይወቅ ይረዳ፤ በረከት ፈንታ መርገምን፣ ስለ ኃጢአት ሥርየት ፈንታም የገሃነም እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
If there be any who disdains this word of the priest or laughs or speaks or stands in the church in an evil manner, let him know and understand that he is provoking to wrath our Lord Jesus Christ, and bringing upon himself a curse instead of a blessing, and will get from God the fire of hell instead of the remission of sin.
ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
ሎተ አምኃ (ጸሎተ ሰላምታ)፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ
የአምኃ ጸሎት (የሰላምታ ጸሎት)፤ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም የሰው ፈቃድ
Prayer of Salutation… Glory to God in heaven and on earth peace, His goodwill toward men.
ልዩ በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተሳዐሙ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድስት
ፍጹም ሰላምና ፍቅር ጸልዩ እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ ሰላምታ እጅ ተንሱ
Pray for the perfect peace and love. Salute one another with a holy salutation.
ርስቶስ አምላክነ ረሥየነ ድልዋነ ከመ ንተሳዐም በበይናቲነ በአምኃ ቅድስት
አምላካችን ክርስቶስ ሆይ እርስ በርሳችን በተቀደሰ ሰላምታ እጅ እንድንነሳ የበቃን አድርገን
Christ our God, make us meet to salute one another with a holy salutation.
ኰቴተ ቊርባን ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስሌነ ወይዕቀባ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ለዓለመ ዓለም አሜን።
የቅዱስ ዲዮስቆሮስ የቁርባን ምስጋና፤ በሁላችንም ላይ ይደር አገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቃት ለዘላለሙ አሜን፤
The Anaphora of St Dioscorus, may his prayer be with us, may he watch over Ethiopia, world without end. Amen.
ግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁም ጋር ይሁን ከመንፈስህ ጋር
The Lord be with you all. And with Thy spirit
እኵትዎ ለአምላክነ። ርቱዕ ይደሉ።
አምላካችንን አመስግኑት፤ እውነት ነው ይገባል
Give Ye thanks unto our God. It is right, it is just.
ልዕሉ አልባቢክሙ። ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ።
ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን
Lift up your hearts. We have lifted them up unto the Lord our God.
ምቅድመ ዓለም . . . ዲያቆን፦ በእንተ ብፁዕ ወቅዱስ . . .
እግዚአብሔር ከዓለም በፊት . . . ዲያቆን፦ ብፁዕ ቅዱስ ስለሚሆን . . .
From before the world and ever after,... Deacon: For the sake of the blessed and holy ...
ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ባርክ ሕዝበከ ክርስቲያን ፍቁራነ በበረከተ ሰማያዊ ወምድራዊ......
ልዩ ሦስትነት የምትሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የሚወደዱ የክርስቶስ ወገኖች የሚሆኑ ሕዝብህን በሰማያውያንና በምድራውያን በረከት ባርክ......
O Holy Trinity, Father and Son and Holy Spirit, bless Thy people, Christians beloved, with blessings heavenly and earthly…
ሐሮሙ እግዚኦ ወተሣሃሎሙ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን
አቤቱ የጳጳሳትን አለቃ ጳጳሳቱን ኤጲስ ቆጶሳቱን ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን የክርስቲያን ወገኖቻችንን ሁሉ ማራቸው ይቅርም በላቸው።
Lord pity and have mercy upon the patriarchs, archbishops, bishops, priest, deacons and all the Christian people.
ማይ ይሰማዕ ወምድርኒ ታጸምእ ወምድረ መሠረታትኒ ይደንግፁ። ዲያቆን፦ እለ ትነብሩ ተንሥኡ።
ሰማይ ይስማ ምድርም ታድምጥ የምድር መሠረቶችም ይደንግጡ። ዲያቆን፦ የተቀመጣችሁ ተነሡ።
Let Heaven hear, the earth listen, and the Foundations of the earth be afraid. Deacon: Ye that are sitting, stand up.
አቡሁ ፈቃድ ወረደ በኪነ ማርያም እንግዳ ኮነ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናሁ ተወለደ። ዲያቆን፦ ኀበ ምስራቅ ነጽሩ።
በአባቱ ፈቃድ ወረደ በሊቃውንት ዘንድ እንግዳ ሆነ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። ዲያቆን፦ ወደ ምስራቅ ተመልከቱ።
The Lord came down through the will of His Father, sojourned in Mary and was born while she was a pure virgin. Deacon: Look to the east.
እንስሳት በረት ተመሰለ የንጉሥንም እጅ መንሻ ተቀበለ ከእናቱ ጡት ምግቡን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ በግልጽ ተመላለሰ እንደ ሰውም ታየ በጥቂቱ አደገ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ።
በእንስሳት በረት ተኛ የንጉሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ፤ በግልጽ ተመላለሰ እንደ ሰውም ታየ በጥቂቱ አደገ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ።
He was laid in the manger of the cattle, received the presents of His kingdom, and wept as infants do, asking for food from the breasts of His mother. He walked openly and appeared like a man, grew little by little and was baptized in Jordan at the age of thirty.
ንደ ሰው ሆኖ ለመጾም በገዳም አደረ ከዲያብሎስ ዘንድ ተፈተነ የጨለማውን መኳንንት በአምላክነቱ ኃይል ሻረ። ዲያቆን፦ ነጽሩ።
እንደ ሰው ሆኖ ለመጾም በገዳም አደረ ከዲያብሎስ ዘንድ ተፈተነ የጨለማውን መኳንንት በአምላክነቱ ኃይል ሻረ። ዲያቆን፦ እናስተውል።
He stayed in the wilderness as a fasting man, was tempted by the Devil and He degraded the rulers of darkness through the power of His divinity. Deacon: Let us give heed.
ውሥኡ፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባኦት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ተቀበሉ፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ የመላ ነው።
Answer Ye. Holy Holy Holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth are full of the Holiness of Thy Glory.
ዝከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ ተዝከረነ እግዚኦ በውስተ ኃይልከ ተዝከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ በከመ ተዝከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።
አቤቱ በመንግሥትህ አስበን አቤቱ በኃይልህ አስበን አቤቱ በመንግሥትህ አስበን ቅዱስ በሆነ መስቀል ላይ ሳለህ በስተቀኝ ያለውን ፈያታዊ ዘየማንን እንደ አስበኸው አቤቱ በመንግሥትህ አስበን።
Remember us, Lord, in Thy kingdom; remember us, Lord, Master, in Thy kingdom; remember us, Lord, in Thy kingdom, as Thou didst remember the thief on the right hand when Thou was on the tree of the Holy Cross.
ንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት። ካህን፦ በይእቲ ሌሊት .....
ቀሳውስት እጆቻችሁን አንሱ፤ ካህን፦ እርሱን በያዙት በዚያች ሌሊት ነውር በሌለባቸው ንጹሐን ክቡራት ብፁዓትም በሚሆኑ እጆቹ ኅብስቱን አነሳ ያዘ፤
Priests, raise up your hands. Priest: In the same night in which they betrayed Him He took bread in His holy, blessed and spotless hands;
አምን ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን። ካህን፦ ወደ አንተ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ አቅንቶ አየ አመሰገነ፤ ባረከ፤ ቆረሰውም።
ይህ እንደሆነ በእውነት እናምናለን፤ ካህን፦ ወደ አንተ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ አቅንቶ አየ አመሰገነ፤ ባረከ፤ ቆረሰውም፤
We believe that this is He, truly we believe. Priest: He looked up to heaven towards you, His Father; gave thanks, blessed and broke;
ወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲሁ ንጹሐን ወይቤሎሙ ንሥኡ ብልዑ ዝንቱ ኅብስት ሥጋየ ውእቱ ዘበእንቲአክሙ ይትፈተት ለስርየተ ኃጢአት።
ንጹሐን ቅዱሳን ለሚሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው፤ ይህ ኅብስት ስለ እናንተ የሚፈተት ሥጋዬ ነው እያለ ንሡ ብሉ አላቸው።
And He gave to His holy disciples and His pure apostles and said unto them: Take, eat, this bread is my body, which will be broken for you for the remission of sin.
ሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን አሜን እናምናለን እንታመናለን ጌታችንና አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን ይህ እርሱ እንደሆነ በእውነት እናምናለን
Amen Amen Amen: We believe and confess, we glorify thee, O our Lord and our God; that this is He we truly believe.
ካዕበ ማየ ምስለ ወይን ጸሊሖ አእኰተ ባረከ ወቀደሰ ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲሁ ንጹሐን ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ ዝንቱ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ዘበእንቲአክሙ ይትከዐው ለስርየተ ኃጢአት።
ዳግመኛም ውኃውን ከወይን ጋራ ቀላቅሎ አመሰገነ ባረከ አከበረ፤ ንጹሐን ቅዱሳን ለሚሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው፤ ይህ ጽዋ ስለ ብዙዎች የሚፈስ ደሜ ነው ንሡ ጠጡ አላቸው።
Again He mixed water with wine, gave thanks, blessed, hallowed and gave it to His holy disciples and His pure apostles and said unto them: take, drink, this cup is my blood which will be shed for you as propitiation for many.
ሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን አሜን እናምናለን እንታመናለን ጌታችንና አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን ይህ እርሱ እንደሆነ በእውነት እናምናለን
Amen amen amen: We believe and confess, we glorify Thee, O our Lord and our God; that this is He we truly believe.
ይሁድ አኃዝዎ ወአቀሙሁ ውስተ ዐውድ ለዘይቀውሙ ቅድሜሁ ኃይለ መላእክት በፍርሃት ወበረዓድ ወሰቀልዎ ዲበ ዕፅ ወቸነከርዎ በቅንዋት ወዘበጥዎ ውስተ ርእሱ በበትር ወወገዝዎ ገቦሁ በኵናት
አይሁድ ያዙት የመላእክት ሠራዊት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የሚቆሙለትን እርሱን በአደባባይ አቆሙት፤ በዕንጨት ላይ ሰቀሉት በችንካር ቸነከሩት፤ ራሱንም በዘንግ መቱት ጎኑን በጦር ወጉት
The Jews took hold of Him and made Him stand in the court, Him before whom the hosts of angels stand in fear and trembling. They crucified Him on the tree, nailed Him with nails, beat Him on the head with sticks, pierced His side with a spear,
ዘአስተዮሙ ለእስራኤል እምኰኵሕ አስተይዎ ሐሞተ ጽሙተ ምስለ ከርቤ በጊዜ ጽምኡ። ዘኢይመውት ሞተ ሞተ ከመ ይስዕሮ ለሞት ሞተ ከመ ያሕይዎሙ ለሙታን በከመ ነገሮሙ ቃል ኪዳን።
ከገደል እምነት ለእስራኤል ያጠጣቸውን በጠማው ጊዜ ከከርቤ ጋር የተቀላቀለ ሐሞትን አጠጡት፤ የማይሞተው እርሱ ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ፤ በቃል ኪዳን ተስፋውን እንደ ነገራቸው።
To Him who gave drink to the Israelites from a rock they gave to drink gall mixed with myrrh in His thirst. The immortal died, died to destroy death, died to quicken the dead as He promised them with the word of covenant.
ዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ ንሴብሐከ ወንትአመነከ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ።
አቤቱ ሞትህንና ልዩ ትንሣኤህንም እንናገራለን ዕርገትህንና ዳግመኛ መምጣትህን እናምናለን፤ እናመሰግንሃለን እናምንሃለን፤ ፈጣሪያችን ሆይ እንማለድሃለን
We proclaim Thy death, Lord, and Thy holy resurrection; we believe in Thy ascension and Thy second advent. We glorify Thee, and confess Thee, we offer our prayer unto Thee and supplicate Thee, O our Lord and our God.
ሜን እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ። ዲያቆን፦ በኵሉ ልብ ናስተበቊዖ ለእግዚአብሔር ከመ ይጸግወነ ኅብረተ መንፈስ ቅዱስ።
አቤቱ ማረን አቤቱ ራራልን አቤቱ ይቅር በለን፤ ዲያቆን፦ በፍጹም ልብ እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን አንድነት ይሰጠን ዘንድ እንለምነው።
Amen; Lord have pity upon us, Lord spare us, Lord have mercy upon us. Deacon: With all the heart let us beseech the Lord our God that he grant unto us the good communion of the Holy Spirit.
ከመ ሀሎ ህልወ ወይሄሉ ለትውልደ ትውልድ ለዓለመ ዓለም።
በፊት እንደነበረ ለዘለዓለሙ ከልጅ ልጅ ይኖራል
As it was, is and shall be unto generations of generations, world without end.
በነ ንኅበር በዝንቱ ቅዱስ መንፈስከ ወፈውሰነ በዝንቱ መሥዋዕት ዘአቅረብነ ለከ ከመ ብከ ንሕየው ለዓለም።
የአንተ በሆነ በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ በዚህም በሥጋው በደሙ አድነን ለዘለዓለሙ ሕያው ሆነን እንኖር ዘንድ
Grant us to be untied through Thy Holy Spirit, and heal us by this oblation that we may live in Thee for ever.
ትባረክ ስሙ ለእግዚአብሔር ወይትባረክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ ለይኩን ለይኩን ቡሩክ ለይኩን።
የእግዚአብሔር ስም ይመስገን በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ይመስገን ጌትነቱም ይመስገን ይሁን ይሁን ይመስገን ይሁን
Blessed be the name of the Lord, and blessed be He that cometh in the name of the Lord, and Let the name of His Glory be blessed. So be it, so be it, so be it blessed.
ኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ። ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት።
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክልን፤ ዲያቆን፦ ለጸሎት ተነሡ።
Send the grace of the Holy Spirit upon us. Deacon: Stand up for prayer.
