Learn Orthodox Stained Glass Logo
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ
ዲያቆን
ገጽ 47
ግዕዝ

እንተ ትዕግሥተ ነፍስ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግወነ ፍጹመ ትዕግሥተ በኵሉ ምንዳቤነ። በእንተ ቅዱሳን ነቢያት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይኅብረነ ምስሌሆሙ።

አማርኛ

በመከራችን ሁሉ እግዚአብሔር ፍጹም ትዕግሥትን ይሰጠን ዘንድ ስለ ነፍሳችን ትዕግሥት እንለምናለን። እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ይቆጥረን ዘንድ ስለ ቅዱሳን ነቢያት እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For patience of soul we beseech, that God may vouchsafe us perfect patience in all our tribulation. For the holy prophets we beseech, that God may number us with them.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 48
ግዕዝ

እንተ አገልጋዮች ሐዋርያት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይኅብረነ ምስሌሆሙ ወይክፍለነ ክፍል ምስሌሆሙ። በእንተ ሰማዕት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግወነ ግብረ ሰማዕትነት ወይኅብረነ ምስሌሆሙ።

አማርኛ

እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ዕድል ፈንታችንን ያደርግልን ዘንድ ስለ ሐዋርያት እንለምናለን። እግዚአብሔር የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the ministering Apostles we beseech, that God may grant us to be well pleasing even as they were well pleasing, apportion unto us a lot with them. For the Holy martyrs we beseech, that God may grant us to perfect the same conversation.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 49
ግዕዝ

እንተ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትነ... ወሊቀ ጳጳሳትነ... ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር በርዝኃነ መዋዕል ይዕቀቦሙ ላዕሌነ ወይጽግዎሙ ቃለ ሃይማኖት በንጽሕና።

አማርኛ

እግዚአብሔር በዕድሜ እንዲጠብቃቸው፣ የእምነትን ቃል በንጽሕና ያስተምሩ ዘንድ ስለ ሊቀ ጳጳሳችንና ስለ ጳጳሳችን እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For our Patriarch and the blessed Archbishop we beseech, that grant them length of days to be over us, that with understanding they may rightly speak the word of faith in purity without spot for that they are the defenders of the church.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 50
ግዕዝ

እንተ ቀሳውስት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ኢያንሥእ እምኔሆሙ መንፈሰ ክህነት ወይጸግዎሙ ረድኤተ ወፍርሃተ እስከ ፍጻሜ።

አማርኛ

እግዚአብሔር የክህነትን ሥልጣን ከእነርሱ እንዳይወስድ፣ ፍርሃቱንና ቅናቱን ይሰጣቸው ዘንድ ስለ ቀሳውስቱ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the priests we beseech, that God may never take from them the spirit of priesthood, and may give them the grace of zeal and fear of Him unto the end and accept their labor.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 51
ግዕዝ

እንተ ዲያቆናት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ግብረ ፍጹመ ወያቅርቦሙ ኀቤሁ በቅድስና ወይዝክር ድካሞሙ ወፍቅሮሙ።

አማርኛ

ዲያቆናቱ አገልግሎታቸውን በንጽሕና ይፈጽሙ ዘንድ፣ ፍቅራቸውንና ድካማቸውን ያስብላቸው ዘንድ ስለ ዲያቆናቱ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the deacons we beseech, that God may grant them to run a perfect course, and draw them high unto Him in holiness, and remember their labor and their love.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 52
ግዕዝ

እንተ ንፍቀ ዲያቆናት ወአናግንስጢስ ወመዘምራን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ፍጹመ ሃይማኖት ወትጋተ።

አማርኛ

እግዚአብሔር የእምነትን ትጋት ይሰጣቸው ዘንድ ስለ ንፍቀ ዲያቆናት፣ ስለ አንባቢዎችና ስለ መዘምራን እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the assistant deacons and the anagnosts and the singers we beseech, that God grant them to perfect the diligence of their faith.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 53
ግዕዝ

እንተ ባልቴታት ወዕጓለ ማውታ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይስምዕ ጸሎቶሙ ወይጸግዎሙ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ወይትወከፍ ጻማሆሙ።

አማርኛ

እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ይሰማ ዘንድ፣ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በልባቸው ያሳድርባቸው ዘንድ ስለ ባልቴቶችና ስለ ድሆች እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the widows and the bereaved we beseech, that God may hear their prayers and vouchsafe them abundantly in their hearts the grace of the Holy Spirit and accept their labor.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 54
ግዕዝ

እንተ ደናግል ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ አክሊለ ድንግልና ወይኩኑ ለእግዚአብሔር ውሉደ ወአዋልደ ወይትወከፍ ጻማሆሙ።

አማርኛ

እግዚአብሔር የድንግልናቸውን ዋጋ ይሰጣቸው ዘንድ፣ ለእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስለ ደናግል እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the virgins we beseech, that God may grant them the crown of virginity, and that they may be unto God sons and daughters and that He may accept their labor.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 55
ግዕዝ

እንተ እለ ይትዓገሡ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይዕቀቦሙ በትዕግሥቶሙ ወይጸግዎሙ ዕሴተ ጻማሆሙ።

አማርኛ

በመታገሣቸው እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይሰጣቸው ዘንድ ስለሚታገሡ ሰዎች እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For those who suffer patiently we beseech, that God grant them to receive their rewards through patience.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 56
ግዕዝ

እንተ ሕዝብ ወሕዝባውያን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይዕቀብ ሃይማኖቶሙ በንጽሕና።

አማርኛ

እግዚአብሔር እምነታቸውን በንጽሕና ይጠብቅላቸው ዘንድ ስለ ሕዝቡና ስለ ምዕመናን እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the laity and faithful we beseech, that God may grant them complete faith which they may keep in purity.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 57
ግዕዝ

እንተ ንኡሰ ክርስቲያን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ዕድለ ሠናየ ወሕፅበተ ዳግም ልደት ወስርየተ ኃጢአት ወይኅትሞሙ በኅትመ ሥላሴ ቅድስት።

አማርኛ

እግዚአብሔር ሁለተኛ መወለድን፣ የኃጢአት ስርየትንና የተባረከ ዕድል ፈንታን ይሰጣቸው ዘንድ፣ በቅድስት ሥላሴ ስም ማኅተምን ያሳድርባቸው ዘንድ ስለ ንኡሰ ክርስቲያን እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the catechumens we beseech, that God may grant them a good portion and the washing of regeneration for the remission of sin, and seal them with the seal of the Holy Trinity.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 58
ግዕዝ

እንተ ሀገርነ ኢትዮጵያ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዋ ሰላመ ለዓለም። በእንተ መኳንንትነ ወእለ ውስተ ሥልጣን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ጥበበ ወፍርሃተ።

አማርኛ

እግዚአብሔር ለዘላለም ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ስለ ሀገራችን ስለ ኢትዮጵያ እንለምናለን። እግዚአብሔር ጥበቡንና ፍርሃቱን ይሰጣቸው ዘንድ ስለ ገዢዎቻችንና ስለ ባለሥልጣናት እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For our country Ethiopia we beseech, that God may give her peace forever. For the rulers and those in authority we beseech, that God may grant them of His wisdom and His fear.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 59
ግዕዝ

እንተ ኵሉ ዓለም ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ያቀልል ሕማሞሙ ወይጸግዎሙ ሠናየ ወዘይበቊዕ።

አማርኛ

እግዚአብሔር ፈቃዱን ያፋጥን ዘንድ፣ ለሁሉም መልካሙንና የሚበጀውን ያስብ ዘንድ ስለ ዓለም ሁሉ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the whole world we beseech, that God should hasten His purpose and put into the mind of all and each to desire that which is good and expedient.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 60
ግዕዝ

እንተ እለ የሐውሩ ፍኖተ በባሕር ወበየብስ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይምራሆሙ በየማነ ምሕረቱ ወያብጽሖሙ ውስተ አብያቲሆሙ በሰላም ወበጤና።

አማርኛ

በውኃና በየብስ በመንገድ የሚሄዱ ሰዎችን እግዚአብሔር በምሕረቱ ቀኝ ይመራቸው ዘንድ፣ በሰላምና በጤና ወደ ቤታቸው ይመልሳቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For them that travel by sea and by land we beseech, that God should guide them with a merciful right hand and let them enter their home in safety and peace.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 61
ግዕዝ

እንተ ርጉባን ወጽሙኣን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ሲሳዮሙ። በእንተ እለ ውስተ ኃዘን ወምንዳቤ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ፍጹመ ናዝዞ።

አማርኛ

ስለ ተራቡትና ስለ ተጠሙት ሰዎች እግዚአብሔር ዕለታዊ ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን። ስለ አዘኑትና ስለ ተከዙት ሰዎች እግዚአብሔር ፍጹም መጽናናትን ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the hungry and the thirsty we beseech, that God should grant them their daily food. For the sad and the sorrowful we beseech, that God may give them perfect consolation

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 62
ግዕዝ

እንተ እለ ውስተ ሞቅሕ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይፍታሕ እስራቶሙ። በእንተ ምርኩሳን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ያብጽሖሙ ውስተ ምድሮሙ በሰላም።

አማርኛ

ስለ ታሰሩት ሰዎች እግዚአብሔር ከእስራታቸው ይፈታቸው ዘንድ እንለምናለን። ስለ ተማረኩት ሰዎች እግዚአብሔር በሰላም ወደ ሀገራቸው ይመልሳቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the prisoners we beseech, that God may loose them from their bonds. For the captives we beseech, that God may restore them to their county in peace.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 63
ግዕዝ

እንተ እለ ተሰዱ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ ትዕግሥተ ወትምህርተ ሠናየ ወይትወከፍ ጻማሆሙ።

አማርኛ

ስለ ተሰደዱት ሰዎች እግዚአብሔር በትምህርቱና በትዕግሥቱ ያጸናቸው ዘንድ፣ ለድካማቸውም ፍጹም ዋጋቸውን ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For those who were sent away we beseech, that God should grant them patience and good instruction, and give them complete reward for their labor.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 64
ግዕዝ

እንተ ድውያን ወሕሙማን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይፈውሶሙ ፍጡነ ወይፈኑ ሎሙ ምሕረተ ወሣሕለ።

አማርኛ

ስለ ታመሙትና ስለ ደከሙት ሰዎች እግዚአብሔር ፈጥኖ ይፈውሳቸው ዘንድ፣ ምሕረቱንና ቸርነቱን ይልክላቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the sick and the diseased we beseech, that God should heal them speedily and send upon them mercy and compassion.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 65
ግዕዝ

እንተ እለ አዕረፉ ውስተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዎሙ መካነ ዕረፍት።

አማርኛ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወገን ስለ ሞቱት ሰዎች እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For those who have fallen asleep in his holy church we beseech, that God may vouchsafe them a place to rest.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 66
ግዕዝ

እንተ እለ አበሱ አበዊነ ወአኃዊነ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ኢያማዕዕዕ ላዕሌሆሙ ወይጸግዎሙ ዕረፍተ ወአድኅኖ እመዓቱ።

አማርኛ

በደል ስላለባቸው ስለ አባቶቻችንና ስለ ወንድሞቻችን እግዚአብሔር ቁጣውን ይመልስላቸው ዘንድ፣ ዕረፍትና ከቁጣው መዳንን ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For those who have sinned, our fathers and our brothers we beseech, that God cherish not anger against them, but grant them rest and relief from His wrath.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 67
ግዕዝ

እንተ ዝናማት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ያውርድ ዝናመ ውስተ መካን ዘይፈቅድ። በእንተ ማያተ አፍላግ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይምላእ እስከ ልኮሙ ወወሰኖሙ።

አማርኛ

በሚሻው ቦታ እግዚአብሔር ዝናቡን ያዘንብ ዘንድ ስለ ዝናብ እንለምናለን። የወንዞችን ውኃ እግዚአብሔር እስከ ልካቸውና እስከ ወሰናቸው ይሞላ ዘንድ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the rains we beseech, that God may send rain on the place that needs it. For the water of the rivers we beseech, that God should fill them unto their due measure and bounds.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 68
ግዕዝ

እንተ ፍሬ ምድር ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይጸግዋ ለምድር ፍሬሃ ለዘርዕ ወለዓጺድ።

አማርኛ

ለመዝራትና ለማጨድ እግዚአብሔር የምድርን ፍሬ ይሰጣት ዘንድ ስለ ምድር ፍሬ እንለምናለን።

እንግሊዝኛ

For the fruits of the earth we beseech, that God may grant to the earth her fruit for sowing and for harvest.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 69
ግዕዝ

እንተ ኵልነ እለ ናስተበቊዕ በጸሎት ከመ እግዚአብሔር ይጼልለነ በቅዱስ መንፈስ ሰላም ወይጸግወነ ጸጋ ወያብርህ አዕይንተ ልብነ ወናቅርብ ጸሎተነ ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ይትወከፍ ጸሎተነ በፈቃዱ።

አማርኛ

በጸሎት የምንማጸንና የምንለምን ሁላችንንም በሰላም መንፈስ ይጋርደን ዘንድ፣ ጸጋውንም ይሰጠን ዘንድ፣ የልባችንንም ዓይኖች ያበራልን ዘንድ፤ ቀርበን እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደ ፈቃዱ ይቀበል ዘንድ እንማጸነው።

እንግሊዝኛ

And all of us who ask and beseech in prayer, may He cover us with the spirit of peace, and give us grace, and enlighten the eyes of our hearts. Let us draw high and ask God to accept our prayers according to His will.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 70
ግዕዝ

ትሣእ እንከ በመንፈስ ቅዱስ እንዘ ንከውን ጽኑዓነ በጸጋሁ ወንትሜካሕ በስሙ ቅዱስ እለ ሕንፁጻን ዲበ መሠረተ ነቢያት ወሐዋርያት ወናቅርብ ጸሎተነ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ ከመ ይትወከፍ ጸሎተነ በፈቃዱ።

አማርኛ

እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ እንነሣ፤ በጸጋው እያደግን፣ በስሙ እየተመካን፣ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ እንታነጽ፤ ቀርበን ጌታ አምላካችን ጸሎታችንን እንደ ፈቃዱ ይቀበል ዘንድ እንለምነው።

እንግሊዝኛ

Let us therefore rise in the Holy Spirit, growing in His grace, with understanding, glorying in His name and built upon the foundation of the prophets and the apostles. Let us draw high and ask Lord God to accept our prayers according to His will.

በ AI ለመማር ይጫኑ