Learn Orthodox Stained Glass Logo
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ
priest_and_congregation
ገጽ 100
ግዕዝ

ፈሥሒ ኦ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ቅድስት ወንጽሕት ሰአሊተ አማን በእንተ እጓለ እመሕያው። ተፈሥሒ።

አማርኛ

በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኚ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ።

እንግሊዝኛ

Rejoice, O Virgin Mary, parent of God, holy and pure, very pleader for the race of mankind. Rejoice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 101
ግዕዝ

አሊ ለነ ቅድመ ክርስቶስ ወልድኪ ከመ ይጸግወነ ስርየተ ኃጢአትነ። አሜን።

አማርኛ

የኃጢአታችንን ስርየት ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ በክርስቶስ ፊት ለምኚልን። አሜን።

እንግሊዝኛ

Plead for us before Christ thy Son, that He may vouchsafe us remission of our sins. Amen.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 102
ግዕዝ

ፈሥሒ ኦ ድንግል ንጽሕት ንግሥት በአማን። ተፈሥሒ። ተፈሥሒ ኦ ትምክህተ ዘመድነ። ተፈሥሒ።

አማርኛ

በእውነት ንግሥት የምትሆኚ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ። የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ።

እንግሊዝኛ

Rejoice, O Virgin pure, very Queen. Rejoice. Rejoice, O pride of our kind. Rejoice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 103
ግዕዝ

ፈሥሒ ኦ ዘወለድኪ ለነ አማኑኤል አምላክነ። ተፈሥሒ።

አማርኛ

አምላካችንን አማኑኤልን የወለድሽልን ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ።

እንግሊዝኛ

Rejoice, O thou that barest for us Emmanuel our God. Rejoice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 104
ግዕዝ

ስእለኪ ከመ ተሐዝኚነ ኦ አማናዊት መስተዓርቅት ቅድመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይገብር ምሕረተ ለነፍሳተነ ወይሥረይ ለነ ኃጢአተነ። አሜን።

አማርኛ

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እውነተኛ አስታራቂ ሆነሽ ታስቢን ዘንድ እንለምንሻለን፤ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግልን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ። አሜን።

እንግሊዝኛ

We ask thee to remember us, O true Mediatrix, before our Lord Jesus Christ that He may have mercy upon our souls and forgive us our sins. Amen.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 105
ግዕዝ

ንቱ ውእቱ ጊዜ ባርኮት ወዝንቱ ውእቱ ጊዜ ዕጣን ኅሩይ ጊዜ ስብሐተ ፈጣሪነ መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ።

አማርኛ

የሚመሰገን ጊዜ ይህ ነው፤ የተመረጠ የዕጣን ጊዜም ይህ ነው፤ ሰውን ወዳጅ መድኃኒታችንን ክርስቶስን ማመስገኛ ነው።

እንግሊዝኛ

This is the time of blessing; this is the time of chosen incense, the time of the praise of our Savior, lover of man, Christ.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 106
ግዕዝ

ርያም ይእቲ ዕጣን ወዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዐዝ እምኵሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ ወአድኃነነ።

አማርኛ

ማርያም ናት ዕጣን፤ ዕጣን እርሱ ነው፤ በማኅፀኗ ያደረ ከታጠበው ዕጣን ሁሉ የሚሸት ነውና፤ የወለደችው መጥቶ አዳነን።

እንግሊዝኛ

Mary is the incense, and the incense is He, because he who was in her womb is more fragrant than all chosen incense. He whom she bare came and saved us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 107
ግዕዝ

ፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ንዑ ንስግድ ሎቱ ወንዕቀብ ትእዛዛቲሁ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጢአተነ።

አማርኛ

ኢየሱስ ክርስቶስ መዓዛ ያለው ሽቱ ነው፤ ኑ እንስገድለት ትእዛዛቱንም እንጠብቅ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ።

እንግሊዝኛ

The fragrant ointment is Jesus Chris. O come let us worship Him and keep His commandments that He may forgive us our sins.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 108
ግዕዝ

ውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል ዘያብጽሓ ውስተ መንግሥት።

አማርኛ

ለሚካኤል ምሕረት ተሰጠው፤ ለገብርኤልም ማብሰር ተሰጠው፤ ለድንግል ማርያምም ወደ መንግሥተ ሰማያት የምትገባበት ሀብት ተሰጣት።

እንግሊዝኛ

To Michael was given mercy, and glad tidings to Gabriel, and a heavenly gift to the Virgin Mary.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 109
ግዕዝ

ውህቦ ክብር ለዳዊት ወጥበብ ለሰሎሞን ወቀረነ ቅብዕ ለሳሙኤል እስመ ውእቱ ይቀብዕ ነገሥተ።

አማርኛ

ለዳዊት ክብር ለሰሎሞንም ጥበብ ለሳሙኤልም ነገሥታትን የቀባ እርሱ ነውና የሽቱ ቀንድ ተሰጠው።

እንግሊዝኛ

To David was given understanding, and wisdom to Solomon, and an horn of oil to Samuel for he was the anointer of kings.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 110
ግዕዝ

ውህቦ መራኁት ለእግዚእነ ጴጥሮስ ወድንግልና ለዮሐንስ ወመልእክት ለእግዚእነ ጳውሎስ እስመ ውእቱ ብርሃነ ቤተ ክርስቲያን።

አማርኛ

ለአባታችን ለጴጥሮስ መክፈቻ ለዮሐንስም ድንግልና ተሰጠው፤ ለአባታችን ለጳውሎስ የቤተክርስቲያን ብርሃን እርሱ ነውና መላእክት ተሰጠው።

እንግሊዝኛ

To our father Peter were given the keys, and virginity to John, and apostleship to our father Paul, for he was the light of the church.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 111
ግዕዝ

ፍረት ምዑዝ ይእቲ ማርያም እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዐዝ እምኵሉ ዕጣን መጽአ ወተሠገወ እምኔሃ።

አማርኛ

መዓዛ ያላት ሽቱ ማርያም ናት፤ በማኅፀኗ ያደረው ከአማኝ ሁሉ የሚበልጥ ነውና መጥቶ ከእርሷ ሰው ሆነ።

እንግሊዝኛ

The fragrant ointment is Mary, for he that was in her womb, who is more fragrant than all incense, came and was incarnate of her.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 112
ግዕዝ

ማርያም ድንግል ንጽሕት ሠምረ አብ ወአሠርገዋ ደብተራ ለማኅደረ ፍቁር ወልዱ።

አማርኛ

ንጽሕት ድንግል ማርያም አብ ወደዳት፤ ከተወደደ ልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ በንጽሕና አስጌጣት።

እንግሊዝኛ

In Mary virgin pure the Father was well-pleased, and he decked her to be a tabernacle for the habitation of his beloved Son.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 113
ግዕዝ

ውህቦ ሕግ ለሙሴ ወክህነት ለአሮን ተውህቦ ዕጣን ኅሩይ ለዘካርያስ ካህን።

አማርኛ

ለሙሴ ሕግ ለአሮንም ክህነት ተሰጠው፤ ለካህኑ ለዘካርያስም የተመረጠ ዕጣን ተሰጠው።

እንግሊዝኛ

To Moses was given the law, and priesthood to Aaron. To Zacharias the priest was given chosen incense.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 114
ግዕዝ

ብተራ ስምዕ ገብርዋ በከመ ነገረ እግዚእ ወአሮን ካህን በመካከላ ያዐርግ ዕጣነ ኅሩየ።

አማርኛ

የምስክር ድንኳን አደረጉት ጌታ እንደተናገረ፤ ካህኑ አሮን በመካከሏ የተመረጠውን ዕጣን ያሳርጋል።

እንግሊዝኛ

They made a tabernacle of testimony according to the word of God; and Aaron the priest, in the midst thereof, made the chosen incense to go up.

በ AI ለመማር ይጫኑ