Learn Orthodox Stained Glass Logo
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ
priest_and_congregation
ገጽ 204
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with Thy spirit

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_deacon
ገጽ 205
ግዕዝ

ሔረ ጥበብ ወዴት ውእቱ? ማኅደራኒ ወዴት ውእቱ? ወሰናኒ ወዴት ውእቱ? ወሰአሊታ ፍኖታ ወዴት ይትረከብ? .... ዲያቆን፦ ጸልዩ።

አማርኛ

የጥበብ አገሯ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው? ወሰኗስ ወዴት ነው? ፈለጓስ ወዴት ይገኛል? .... ዲያቆን፦ ጸልዩ።

እንግሊዝኛ

"Prayer of Fraction" Where is the country of Wisdom, where is its abode, where is its province, and where can the trace of its way be found? .... Deacon: Pray ye.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 206
ግዕዝ

ቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድርኒ ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ በከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለእለ አበሱ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

አማርኛ

አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን የዕለት ምግባችንን ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል ምስጋናም ለዘለዓለሙ አሜን።

እንግሊዝኛ

Our Father who art in heaven, hallowed be Thy name, Thy kingdom come, Thy will be done on earth as it is in heaven; give us this day our daily bread, and forgive us our trespasses as we forgive them that trespass against us, and lead us not into temptation but deliver us and rescue us from all evil; for Thine is the kingdom, the power and the glory for ever and ever.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 207
ግዕዝ

ከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ (፫ ጊዜ)

አማርኛ

አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ ኃጢአታችን አይደለም (፫ ጊዜ)

እንግሊዝኛ

According to Thy mercy, our God, and not according to our sins. (three times)

በ AI ለመማር ይጫኑ