Learn Orthodox Stained Glass Logo
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ
deacon_and_congregation
ገጽ 71
ግዕዝ

ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።

አማርኛ

ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን

እንግሊዝኛ

Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 72
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with Thy spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 73
ግዕዝ

ስተብቊዕ (፫ ጊዜ)፤ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፫ቱ አሐዱ (፫ ጊዜ)

አማርኛ

እንስገድ (፫ ጊዜ)፤ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ሲሆኑ አንድ ለሆኑት እንሰግዳለን (፫ ጊዜ)

እንግሊዝኛ

Let's worship (to be repeated thrice). The Father and the Son and the Holy Spirit, three in one. (to be repeated thrice)

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 74
ግዕዝ

ላም ለኪ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅደረ መለኮት

አማርኛ

ሰላም ላንቺ ይሁን፤ የመለኮት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

እንግሊዝኛ

Peace be unto thee: Holy church, dwelling-place of the Godhead.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 75
ግዕዝ

እሊ ለነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ አንቲ ውእቱ፦

አማርኛ

ለምኚልን፤ አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም፤ አንቺ ነሽ፦

እንግሊዝኛ

Ask for us: Virgin Mary, mother of God, Thou art:

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 76
ግዕዝ

ዕጠንት ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት ቡሩክ ዘነሥአ እመቅደስ

አማርኛ

ብሩክ ከአምልኮ ቤት የተቀበላትን የእሳት ፍም የተሸከምሽ የወርቅ ጥና አንቺ ነሽ፤

እንግሊዝኛ

the golden censer which didst bear the coal of fire which the blessed took from the sanctuary,

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 77
ግዕዝ

ይሠሪ ኃጢአተ ወይደመስስ ጌጋየ ዘውእቱ ቃለ እግዚአብሔር ዘተሰብአ እምኔኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ ወመሥዋዕተ ሥሙረ።

አማርኛ

ኃጢአትን የሚያስተሰርይና በደልን የሚያጠፋ፤ እሱም ካንቺ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ራሱን ለዓለሙ ሁሉ መዳን መዓዛው ያማረ መሥዋዕት አድርጎ ለአባቱ ያቀረበ።

እንግሊዝኛ

and which forgiveth sin and blotteth out error, who is God's Word that was made man from thee, who offered Himself to his Father for incense and an acceptable sacrifice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 78
ግዕዝ

ሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስከ ቅዱስ ማሕየዊ እስመ መጻእከ ወአድኃንከነ።

አማርኛ

ክርስቶስ ሆይ፤ ከቸር ሰማያዊ አባትህና ሕይወትን ከሚሰጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም እንሰግድልሃለን፤ መጥተህ አድነኸናልና።

እንግሊዝኛ

We worship Thee, Christ, with thy good heavenly Father and thy Holy Spirit, the life-giver, for Thou didst come and save us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
deacon_and_congregation
ገጽ 79
ግዕዝ

ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።

አማርኛ

ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን

እንግሊዝኛ

Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 80
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with Thy spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 81
ግዕዝ

ብሐት ወክብር ለሥላሴ ቅዱስ ይደሉ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በኵሉ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።

አማርኛ

ለቅዱስ ሥላሴ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን

እንግሊዝኛ

Glory and honor are meet to the Holy Trinity, the Father and the Son and the Holy Spirit at all times. Both now and ever and world without end. Amen

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 82
ግዕዝ

ባብ ዘመልእክተ ጳውሎስ ሐዋርያ ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ቀዳማይ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩።

አማርኛ

ከቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው አንደኛው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩ ይነበባል።

እንግሊዝኛ

Reading the 1st. Epistle of St. Paul the Apostle to the Corinthians 15:1

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 83
ግዕዝ

ዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሠናይ መልእክተኛ ፈዋሴ ድውያን ዘተወክፈ አክሊለ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ከመ ያድኅን ነፍሳተነ በብዝኃ ምሕረቱ ወበሣሕሉ በእንተ ስሙ ቅዱስ።

አማርኛ

የአክሊልን ቅቡል የሆንክ የታመሙትን የምትፈውስ የክርስቶስ መልእክተኛ የሆንክ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሆይ፤ በምሕረቱ ብዛት ነፍሳችንን ያድን ዘንድ ስለ እኛ ለምንልን።

እንግሊዝኛ

Holy Apostle Paul, good messenger, healer of the sick, who hast received the crown, ask and pray for us in order that he may save our souls in the multitude of his mercies and in his pity for his holy name's sake.

በ AI ለመማር ይጫኑ
deacon_and_congregation
ገጽ 84
ግዕዝ

ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።

አማርኛ

ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን

እንግሊዝኛ

Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 85
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with thy spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 86
ግዕዝ

ባብ ዘመልእክተ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ሐዋርያ ቀዳማይ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩። ኦ አኃውየ ኢታፍቅሩሃ ለዛቲ ዓለም ወኢዘውስቴታ እስመ ዓለምኒ የኃልፍ ወፍትወታኒ የኃልፍ ኵሉ ኃላፊ ውእቱ።

አማርኛ

የዮሐንስ ሐዋርያ መጀመሪያ መልእክት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩ ይነበባል። ወንድሞቼ ሆይ ይህንን ዓለም አትውደዱ በዓለሙ ውስጥ ያለውንም። ዓለሙ ያልፋል ፈቃዱም ያልፋል ሁሉም ኃላፊ ነውና።

እንግሊዝኛ

Reading the 1st. Epistle of John 1:1

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 87
ግዕዝ

ዱስ ሥሉስ ዘዕሩይ ሕላዌከ ዕቀብ ማኅበረነ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን አርዳኢከ ናዝዘነ በምሕረትከ በእንተ ስምከ ቅዱስ።

አማርኛ

በባሕርይህ አንድ የምትሆን ልዩ ሦስትነት ሆይ፤ ስለተመረጡት ቅዱሳን ደቀ መዛሙርትህ ስትል አንድነታችንን ጠብቅ፤ ስለ ቅዱስ ስምህም በቸርነትህ አጽናን።

እንግሊዝኛ

Holy con substantial Trinity, preserve our congregation for Thy holy elect disciples' sake: comfort us in Thy mercy, for Thy holy name's sake.

በ AI ለመማር ይጫኑ
deacon_and_congregation
ገጽ 88
ግዕዝ

ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።

አማርኛ

ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን

እንግሊዝኛ

Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 89
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with Thy spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 90
ግዕዝ

ባብ ዘግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፩። መልአ ወተለዐለ ቃለ እግዚአብሔር ወበዝኃ ውስተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወአዕላፈ አዕላፋት እለ አመኑ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሎቱ ስብሐት ለዓለመ ዓለም አሜን።

አማርኛ

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፩ ይነበባል። የእግዚአብሔር ቃል ፈጽሞ ሞላ ከፍ ከፍም አለ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በዛ ተጨመረ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ምዕመናን በዙ ለዘላለሙ አሜን።

እንግሊዝኛ

Reading the Acts of the Apostles 23:1

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 91
ግዕዝ

ዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ አምላክ አብ አኃዜ ኵሉ

አማርኛ

ሁሉን የያዝህ አብ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ነህ

እንግሊዝኛ

Holy Holy Holy art Thou, only-begotten Son,

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 92
ግዕዝ

ዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ወልድ ዋሕድ ዘአንተ ቃለ አብ ሕያው

አማርኛ

ሕያው የአብ ቃል የምትሆን ወልድ ዋሕድ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ነህ።

እንግሊዝኛ

Holy Holy Holy art Thou, only-begotten Son, who art the Word of the living Father.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 93
ግዕዝ

ዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ መንፈስ ቅዱስ ዘተአምር ኵሎ

አማርኛ

ሁሉን የምታውቅ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ነህ።

እንግሊዝኛ

Holy Holy Holy art Thou, Holy Spirit who knowst all things.

በ AI ለመማር ይጫኑ
deacon_and_congregation
ገጽ 94
ግዕዝ

ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።

አማርኛ

ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን

እንግሊዝኛ

Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 95
ግዕዝ

ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር

እንግሊዝኛ

Peace be unto you all. And with thy spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 96
ግዕዝ

ፈሥሒ ኦ ዘእምኔኪ ንስእል ድኅነተ ኦ ቅድስት ምልዕተ ክብር። ተፈሥሒ።

አማርኛ

ደኅንነትን የምንለምንብሽ ክብርን የተሞላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ።

እንግሊዝኛ

Rejoice, O thou of whom we ask healing, O holy full of honor. Rejoice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 97
ግዕዝ

ንግል ወላዲተ አምላክ እመ ክርስቶስ አዕርጊ ጸሎተነ ውስተ አርያም ኀበ ፍቁር ወልድኪ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጢአተነ። አሜን።

አማርኛ

ሁልጊዜ ድንግል የምትሆኚ አምላክን የወለድሽ የክርስቶስ እናት ሆይ፤ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሳርጊ። አሜን።

እንግሊዝኛ

Ever-Virgin, parent of God, mother of Christ, offer up our prayer on high to thy beloved Son that He may forgive us our sin. Amen.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 98
ግዕዝ

ፈሥሒ ኦ ዘወለድኪ ለነ ብርሃነ ጽድቅ አማናዊ ክርስቶስ አምላክነ። ተፈሥሒ።

አማርኛ

በእውነት የእውነት ብርሃን የሚሆን አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን (ንጽሕት) ሆይ ደስ ይበልሽ። ደስ ይበልሽ።

እንግሊዝኛ

Rejoice, O thou who didst bear for us the very light of righteousness, even Christ our God. Rejoice.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 99
ግዕዝ

ጽሕት ድንግል ሰአሊ ለነ ኀበ እግዚእነ ከመ ይገብር ምሕረተ ለነፍሳተነ ወይሥረይ ለነ ኃጢአተነ። አሜን።

አማርኛ

ንጽሕት ድንግል ሆይ፤ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግ ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ ወደ ጌታችን ለምኚልን። አሜን።

እንግሊዝኛ

O Virgin pure, plead for us unto our Lord that He may have mercy upon our souls and forgive us our sin. Amen.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 240
ግዕዝ

በኒ እገብር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አስተርኢ በስብሐቲከ ወአሕየው ላዕለ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ፤

አማርኛ

በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ አፈራ ዘንድ ስጠኝ፤ የአንተንም ፈቃድ እየሠራሁ እኖር ዘንድ ስጠኝ፤

እንግሊዝኛ

Grant me to bring forth fruit that shall be well pleasing unto Thee, to the end that I may appear in Thy glory and live unto Thee doing Thy will.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 241
ግዕዝ

ተአምኖ እጼውዐከ አብ ወእጼውዕ መንግሥተከ ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ ባዕሌነ እስመ ኃያል አንተ እኩት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም

አማርኛ

በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ፤ አቤቱ ስምህ በእኛ ላይ ይመስገን፤ ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ

እንግሊዝኛ

In faith, I call upon Thee, Father, and call upon Thy Kindom; hallowed, Lord, be Thy name upon us, for mighty art Thou, praised and glorious, and to Thee be glory, world without end.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 242
ግዕዝ

ስመ ኃያል አንተ እኩት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም

አማርኛ

ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ

እንግሊዝኛ

... for Mighty art Thou, praised and glorious, and to Thee be Glory, for ever and ever.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 243
ግዕዝ

አኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ ከመ ለሕይወተ ነፍስ ይኩነነ ፈውሰ ዘተመወነ ንስእል ወንትመሐፀን እንዘ ንሴብሕ ለእግዚአብሔር አምላክነ።

አማርኛ

ሥጋውን ደሙን ተቀብለን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ከነፍሳችን አፈዋወር መድኃኒት ይሆን ዘንድ የተቀበልን እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እያመሰገንን እንለምናለን፤ አደራም እንላለን

እንግሊዝኛ

We thank God for that we have partaken of His Holy things; we pray and trust that that which we have received may be healing for the life of the soul while we glorify the Lord our God.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 244
ግዕዝ

ልዕለከ ንጉሥየ ወአምላክየ ወእባርክ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።

አማርኛ

ንጉሤና ፈጣሪዬ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህንም ለዘላለሙ አመሰግናለሁ

እንግሊዝኛ

I will extol Thee, my King and my God, and I will bless Thy name for ever and ever.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 245
ግዕዝ

ቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።

አማርኛ

በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን

እንግሊዝኛ

Our Father Thou art in heaven, lead us not, Lord, into temptation.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 246
ግዕዝ

መጦነ እምሥጋሁ ቅዱስ ወእምደሙ ክቡር ለክርስቶስ

አማርኛ

ከክርስቶስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ ተቀበልን

እንግሊዝኛ

We have received of the Holy Body and the precious Blood of Christ.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 247
ግዕዝ

ሎ አሚረ እባርከከ ወእሴብሕ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።

አማርኛ

ዘወትር አመሰግንሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህን ለዘላለሙ አመሰግናለሁ

እንግሊዝኛ

Every day will I bless Thee, and I will praise Thy name for ever and ever.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 248
ግዕዝ

ቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።

አማርኛ

በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን

እንግሊዝኛ

Our Father Thou art in heaven, lead us not, Lord, into temptation.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 249
ግዕዝ

ናእኵቶ ይደልወነ ከመ ንሳተፍ ምሥጢረ ክብርተ ወቅድስት

አማርኛ

ክብርት ቅድስት የምትሆን ምስጢርን እንካፈል ዘንድ ለበቃን እናመሰግነው ይገባል

እንግሊዝኛ

And let us give thanks unto him that make us meet to communicate in the precious and holy mystery.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 250
ግዕዝ

ብሐተ እግዚአብሔር ይናገር አፉየ ወኵሉ ዘሥጋ ይባርክ ለስሙ ቅዱስ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።

አማርኛ

አንደበቴ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤ የሥጋ ፍጥረትም ሁሉ ቅዱስ የሚሆን ስሙን ያመሰግናል ለዘላለሙ

እንግሊዝኛ

My mouth shall speak the praise of the Lord, and let all flesh bless His Holy name for ever and ever.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 251
ግዕዝ

ቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።

አማርኛ

በሰማይ ያለህ አባታችን ሆይ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን

እንግሊዝኛ

Our Father Thou art in heaven, lead us not, Lord, into temptation.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_deacon
ገጽ 252
ግዕዝ

ግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልደዋለን... ዲያቆን፦ ጸልዩ።

አማርኛ

ደግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልደዋለን... ዲያቆን፦ ጸልዩ።

እንግሊዝኛ

Again we supplicate the almighty God, Father of our Lord and our Saviour Jesus Christ… Deacon: Pray ye.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 253
ግዕዝ

ዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ፤ አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝህ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ

አማርኛ

አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ፤ አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝህ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ

እንግሊዝኛ

Yea Lord, Thou art the God of all. Yea Lord, Thou art the King of all. Yea Lord, Thou art the Almighty. Yea Lord, Thou art the Governor of all. Yea Lord, Thou art the Savior of all.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 254
ግዕዝ

ዎን አቤቱ የሁሉ ገዢ ነህ፤ አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ

አማርኛ

አዎን አቤቱ የሁሉ ገዢ ነህ፤ አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ፤ አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ

እንግሊዝኛ

Yea Lord, Thou art the Judge of all. Yea Lord, Thou art the Life giver of all. Yea Lord, Thou art the Keeper of all. Yea Lord, Thou art the Nourisher of all.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 255
ግዕዝ

ልጅህን ሥጋ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ እንዳደረግህ ያንተን መሢሕ ደምም ከእኛ ደም ጋር አንድ እንዳደረግህ እንዲሁ አንተን መፍራትን በልቦናችን፤ በጎ አምልኮትህንም በሕሊናችን ጨምር

አማርኛ

የልጅህን ሥጋ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ እንዳደረግህ ያንተን መሢሕ ደምም ከእኛ ደም ጋር አንድ እንዳደረግህ እንዲሁ አንተን መፍራትን በልቦናችን፤ በጎ አምልኮትህንም በሕሊናችን ጨምር

እንግሊዝኛ

As Thou didst join the body of Thy Son with our body, and Thou didst mix the blood of Thy Messiah with our blood, so put Thy fear in our heart and the beauty of Thy worship in our mind.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 256
ግዕዝ

ጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፤ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፤ በሥጋ መንገድም እንሄዳለን፤ አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፤ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፤ የመንፈስንም መንገድ ምራን

አማርኛ

ሥጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፤ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፤ በሥጋ መንገድም እንሄዳለን፤ አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፤ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፤ የመንፈስንም መንገድ ምራን

እንግሊዝኛ

We who are carnal, mind the things of the flesh and do the works of the flesh and walk in the way of the flesh. But do thou teach us the work of the Spirit and make us understand the law of the Spirit and lead us to the way of the Spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ካህን
ገጽ 257
ግዕዝ

ኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና፤ ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሣ ትወዳቸዋለህ፤ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ

አማርኛ

እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና፤ ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሣ ትወዳቸዋለህ፤ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ

እንግሊዝኛ

Because if Thou pity us, we sinners, then Thou wilt be called compassionate. Thou pities the righteous because of their works and dost recompense them according to their righteousness.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 258
ግዕዝ

ቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይድረስልን፤ ወደ አንተ እንጮሃለን፤ ወደ አንተ እናለቅሳለን፤ ወደ አንተ እንማለላለን ለዘላለሙ፤ ሕዝብ፦ አሜን

አማርኛ

የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይድረስልን፤ ወደ አንተ እንጮሃለን፤ ወደ አንተ እናለቅሳለን፤ ወደ አንተ እንማለላለን ለዘላለሙ፤ ሕዝብ፦ አሜን

እንግሊዝኛ

Remember not against us former iniquities: let Thy tender mercies, O God, speedily prevent us. Towards Thee we cry, towards Thee we weep, Thee we entreat, world without end. Congregation: Amen

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 259
ግዕዝ
[

ስዕለ ማርያም]

አማርኛ

[የእመቤታችን ምስል በጸጥታ ጊዜ ይታያል]

እንግሊዝኛ

[St. Mary Icon Displayed for Silent Worship]

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 260
ግዕዝ

ባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ መንግሥትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ እንዲሁ በምድር ሰላምን ስጠን ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግባችንን በደላችንንም ይቅር እንድትለን ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና ኃይልና ምስጋና መንግሥትም ያንተው ናት አሜን ለዘለዓለም ይሁንልን ሕይወት

አማርኛ

አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ መንግሥትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ እንዲሁ በምድር ሰላምን ስጠን ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግባችንን በደላችንንም ይቅር እንድትለን ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና ኃይልና ምስጋና መንግሥትም ያንተው ናት አሜን ለዘለዓለም ይሁንልን ሕይወት

እንግሊዝኛ

Our Father who art in heaven, hallowed be Thy name... [Amharic background hymn variant of the Lord's Prayer]

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 261
ግዕዝ

መቤቴ ማርያም ሆይ (፪ ጊዜ) በመልአኩ ገብርኤል ሰላምታ እንደተነገረሽ ሰላም እንላለን እኛም ልጆችሽ (፪ ጊዜ) በሐሳብሽ ድንግል ነሽ (፪ ጊዜ) በሥጋሽም ድንግል ነሽ የልዑል እናቱ ደግሞም የአሸናፊ ማኅበራችንን በእውነት ደግፊ (፪ ጊዜ) ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ (፪ ጊዜ) የተባረክሽ ነሽ ብሩክ ከሚባለው ከማኅፀንሽ ፍሬ ጸጋን እንዲያድለን ለምኚልን ዛሬ (፪ ጊዜ)

አማርኛ

እመቤቴ ማርያም ሆይ (፪ ጊዜ) በመልአኩ ገብርኤል ሰላምታ እንደተነገረሽ ሰላም እንላለን እኛም ልጆችሽ (፪ ጊዜ) በሐሳብሽ ድንግል ነሽ (፪ ጊዜ) በሥጋሽም ድንግል ነሽ የልዑል እናቱ ደግሞም የአሸናፊ ማኅበራችንን በእውነት ደግፊ (፪ ጊዜ) ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ (፪ ጊዜ) የተባረክሽ ነሽ ብሩክ ከሚባለው ከማኅፀንሽ ፍሬ ጸጋን እንዲያድለን ለምኚልን ዛሬ (፪ ጊዜ)

እንግሊዝኛ

O Our Lady Mary, with the salutation of Gabriel... [Amharic devotional Mary hymn]

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 262
ግዕዝ

ጋና ክብርን የተሞላሽ ሆይ (፪ ጊዜ) ደስ ይበልሽ ያወርድ የነበረው ለእስራኤል መና ቸሩ ፈጣሪያችን ካንቺ ጋር ነውና (፪ ጊዜ) ለምኚ ኢየሱስን ይቅር እንዲለን (፪ ጊዜ) በደላችንን የኃጢአት ባርነት ከእኛ እንዲወጣ ተማፅነንብሻል እንድትሆኚን ተስፋ (፪ ጊዜ) አሜን ....

አማርኛ

ጸጋና ክብርን የተሞላሽ ሆይ (፪ ጊዜ) ደስ ይበልሽ ያወርድ የነበረው ለእስራኤል መና ቸሩ ፈጣሪያችን ካንቺ ጋር ነውና (፪ ጊዜ) ለምኚ ኢየሱስን ይቅር እንዲለን (፪ ጊዜ) በደላችንን የኃጢአት ባርነት ከእኛ እንዲወጣ ተማፅነንብሻል እንድትሆኚን ተስፋ (፪ ጊዜ) አሜን ....

እንግሊዝኛ

O full of grace and honor... [Amharic devotional Mary hymn continued]

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 263
ግዕዝ

ድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በአደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርክክሙ። ሕዝብ፦ አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ በአደ ገብሩ ካህን።

አማርኛ

በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤ አገልጋይ በሚሆን በካህኑ እጅ ይባርካችሁ ዘንድ፤ ሕዝብ፦ አሜን እግዚአብሔር በካህኑ እጅ ይባርከን።

እንግሊዝኛ

Bow your heads in front of the Lord our God, that He may bless you at the hand of His servant the priest. People: Amen, may He bless us at the hand of His servant the priest.

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 264
ግዕዝ

ሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ወይሣሃለነ። ካህን፦ ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝበከ ወባርክ ርስተከ ......

አማርኛ

አሜን እግዚአብሔር ይባርክን ይቅርም ይበለን፤ ካህን፦ አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ......

እንግሊዝኛ

Amen, God bless us and have mercy upon us. Priest: O Lord, save Thy people and bless Thine inheritance…

በ AI ለመማር ይጫኑ
priest_and_congregation
ገጽ 265
ግዕዝ

ግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።

አማርኛ

እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ከመንፈስህ ጋራ

እንግሊዝኛ

The Lord be with you all. And with Thy spirit

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 266
ግዕዝ

ሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ለእለ ንቀውም በሰላም ሥጋከ ወደመከ ዘተመጦነ ለስርየተ ኃጢአት ይኩነነ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ከመ ንኪድ ኵሎ ኃይለ ጸላኢ።

አማርኛ

አሜን እግዚአብሔር እኛን አገልጋዮቹን በሰላም ይባርከን፤ የተቀበልነውን ሥጋህና ደምህን ለሥርየት ይሁንልን፤ የጠላትን ኃይል ሁሉ በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ አሰልጥነን

እንግሊዝኛ

Amen, God bless us His servants in peace. May the Body and Blood we have received be for the remission of sins, and empower us through the Holy Spirit to trample on all the power of the enemy.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 267
ግዕዝ

ረከተ እዴከ ቅድስት እንተ ምልዕተ ምሕረት ንሴፎ ኵልነ አርሕቀነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ ወዲበ ኵሉ ምግባረ ሰናይ ደምረነ ቡሩክ ዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ።

አማርኛ

ምሕረትን የተሞላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን ተስፋ እናደርጋለን፤ ከክፉ ሥራ ሁሉ አርቀን፤ በበጎውም ሥራ ሁሉ አንድ አድርገን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙንም የሰጠን ብሩክ ነው

እንግሊዝኛ

Through the blessing of Thy holy hand which is full of mercy, we wait for the hope of us all. Keep us from every evil work and unite us in every good work. Blessed is He who gave us His holy Body and His precious Blood.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ሕዝብ
ገጽ 268
ግዕዝ

ጋ ነሣእና ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ መስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ኪያከ ነአኵት እግዚኦ ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ።

አማርኛ

ጸጋን ተቀበልን ሕይወትህንም በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ኃይል አገኘን፤ አቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ጸጋን ተቀበልን አንተን እናመሰግንሃለን

እንግሊዝኛ

We have received of Thy grace and found life through the power of His cross. O Lord, we render Thee thanks after receiving the grace of the Holy Spirit.

በ AI ለመማር ይጫኑ
ዲያቆን
ገጽ 269
ግዕዝ

ትዉ በሰላም

አማርኛ

በሰላም ወደ ቤታችሁ ግቡ

እንግሊዝኛ

Go in peace.

በ AI ለመማር ይጫኑ