ውልጦሙ ለዝንቱ ኅብስት ከመ ይኩን ሥጋከ ንጹሐ ወለዝንቱ ጽዋዕኒ ከመ ይኩን ደመከ ክቡረ ወይኩን ለኵልነ ለተረክቦ ማሕየዊ ለሕይወተ ነፍስ ወሥጋ ወመንፈስ።
ይህንን እንጀራ ንጹሕ ሥጋህ ይሆን ዘንድ ለውጠው፤ በዚህ ጽዋ ውስጥ የተቀዳውንም ወይን የከበረ ደምህ ይሆን ዘንድ ለውጠው፤ ለሁላችንም ለነፍሳችን፣ ለሥጋችንና ለሕሊናችንም ፈውስና መዳን ይሆን ዘንድ ይቅረብ።
And change this bread to become Thy pure body, and what is mingled in this cup to become Thy precious blood, let them be offered for us all for healing and for the salvation of our soul and our body and our spirit.
ስመ አንተ ውእቱ ንጉሠ ኵልነ ክርስቶስ አምላክነ ወለከ ንፌኑ ስብሐተ ወዕበየ ወስግደተ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ዘዕሩይ ምስሌከ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
የሁላችን ንጉሥ ክርስቶስ አምላካችን ሆይ፤ አንተ ነህ፤ ለአንተም ከቸር ሰማያዊ አባትህና ሕይወትን ከሚሰጥ ካንተ ጋር በትክክል ከሚተካከል ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ምስጋናን፣ ክብርንና ስግደትን እንልካለን፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Thou art the King of us all, Christ our God, and to Thee we send up high praise and glory and worship, with Thy good heavenly Father and the Holy Spirit, the life giver, who is co-equal with Thee, both now and ever and world without end. Amen.
ቲ ይእቲ ሥርዓተ አበዊነ ሐዋርያት ኢያንብር ሰብእ ውስተ ልቡ ቂመ ወበቀለ ወኢቅናተ ወኢጽልአ ላዕለ ቢጹ ወላዕለ መኑሂ እምሰብእ።
ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው፤ ማንም በልቡ ቂምና በቀልን፣ ቅናትንና ጥላቻን በባልንጀራው ላይ፣ በሌላም በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ።
This is the order of our fathers the Apostles: Let none Keep in his heart malice or revenge or envy or hatred towards his neighbor, or towards any other body.
ግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት። ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ። (ይስግዱ)
በፍርሃት ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ አቤቱ በፊትህ እንሰግዳለን፣ እናመሰግንሃለንም። (ስግደት)
Worship the Lord with fear. Before Thee, Lord, we worship, and Thee do we glorify. (bow)
እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋሕድ ወልደ አብ ቃለ እግዚአብሔር አብ ዘበሕማምከ ማሕየዊ ወመድኃኒ ሰበርከ ኵሎ አእሠርተ ኃጢአትነ ዘነፋሕከ ውስተ ገጸ ሐዋርያቲከ ቅዱሳን ወአርዳኢከ ንጹሐን ወትቤሎሙ ንሥኡ መንፈሰ ቅዱሳ ዘኃደግሙ ሎሙ ኃጢአቶሙ ይኅደግ ሎሙ ወዘአኃዝክሙ ሎሙ ይእኃዝ...
የወልድ የፍታት ጸሎት፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአብ ቃል የሆንክ አንድ ልጅ፤ በሕይወት ሰጪና በማዳን መከራህ የኃጢአታችንን ማሰሪያ ሁሉ የሰበርክ፤ በተቀደሱ ደቀ መዛሙርትህና በንጹሐን አገልጋዮችህ ፊት እፍ ያልህባቸውና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቅር ይባሉላቸዋል፤ ይቅር ያላላችኋቸውም አይቀሩላቸውም ያልካቸው።
The Absolution of the son. Master, Lord Jesus Christ, the Only-begotten Son, the Word of God the Father, who hast broken off from us all the bonds of our sins through Thy life-giving and saving sufferings, who didst breathe upon the face of Thy holy disciples and pure ministers saying to them: Receive the Holy Spirit: whatsoever man's sins ye remit they are remitted unto them, and whatsoever sins ye retain they are retained:
ንተ ይእዜኒ እግዚኦ ወሀብኮሙ ክህነተ ለአርዳኢከ ንጹሐን እለ ይገብሩ ግብረ ክህነት በኵሉ ጊዜ ውስተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንከ ከመ ይስረዩ ኃጢአተ ዲበ ምድር ወይእስሩ ወይፍትሑ ኵሎ ማዕሠረ ዓመፃ ወካዕበ ናስተበቊዕ እምነ ኂሩትከ ኦ መፍቀሬ ሰብእ በእንተ እለ ያበውኡ እለ ይገብሩ ...
አሁንም ጌታ ሆይ በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ሁል ጊዜ የክህነትን አገልግሎት ይሠሩ ዘንድ ለንጹሐን አገልጋዮችህ ክህነትን የሰጠሃቸው፤ በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርዩ ዘንድ፣ የክፋትንም ማሰሪያ ሁሉ ያስሩና ይፈቱ ዘንድ፤ ዳግመኛም ሰውን ከምትወድ ከበጎነትህ እንለምንሃለን፤ ስለምንወዳቸው ስለ ወንዶቹና ስለ ሴቶቹ አገልጋዮችህ፣ ስለ አባቶቼ፣ ስለ ወንድሞቼና ስለ እህቶቼ፣ ስለ እኔም ስለ ደካማው አገልጋይህ በተቀደሰው መሠዊያህ ፊት ራሳቸውን ስላዘነበሉት ሰዎች እንለምንሃለን።
Thou therefore, O Lord, hast now granted the priesthood to Thy pure ministers that do the priests; office at all times in Thy holy church that they may remit sin on earth, may bind and loosen all the bonds of iniquity. Now again we pray and entreat of Thy goodness, O lover of man, on behalf of these Thy servants and handmaids, my fathers and my brothers and my sisters, and also on my own behalf, on me Thy feeble servant, and on behalf of them that bow their heads before Thy holy altar:
አጽንዖሙ ለኵሎሙ እለ አጽነኑ አርእስቲሆሙ ቅድመ መቅደስከ ቅዱስ አደው ሎሙ ፍኖተ ምሕረትከ ሰብር ወምትርት ኵሎ ማዕሠረ ኃጢአቶሙ እመሂ አበሱ ኀቤከ እግዚኦ በአእምሮ እመሂ በኢያእምሮ እመሂ በጕሕሉት እመሂ በሕሊና እኩይ እመሂ በግብር እመሂ በነቢብ እስመ አንተ ታአምር ድካሞ ለሰብእ...
የምሕረትህን መንገድ አዘጋጅልን፤ የኃጢአታችንን ማሰሪያ ሁሉ ቁረጥልን፤ አቤቱ አውቀን ወይም ሳናውቅ የሠራነውን፣ በሽንገላ ወይም በክፉ ልብ ቢሆን፣ በሥራም ሆነ በንግግር ወይም በሕሊና ማነስ የሠራነውን፤ አንተ የሰውን ድካም ታውቃለህና፤ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆንክ ቸሩና ሰውን የምትወድ አምላክ ሆይ፤ አቤቱ የኃጢአታችንን ስርየት ስጠን፤ ባርከን፣ ቀድሰን፣ ነጻም አውጣን፤ ሕዝብህንም ሁሉ ፍታቸው፤ በስምህ ፍርሃትም ሙሉን፤ ቅዱስ ፈቃድህንም በመሥራት አጽናን።
prepare for us the way of Thy mercy, break and sever all the bonds of our sins, whether we have trespassed against Thee, O Lord, wittingly or unwittingly or in deceit or in evilness of heart, whether in deed or in work or through smallness of understanding, for Thou knowest the feebleness of man. O good lover of man and Lord of all creation, grant us, O Lord, forgiveness of our sins, bless us and purify us and set us free and absolve all Thy people and fill us with the fear of Thy name, and establish us in the doing of Thy holy will.
ካዕበ ናስተበቊዕ እምነ ኂሩትከ ኦ መፍቀሬ ሰብእ በእንተ እለ ያበውኡ እለ ይገብሩ... (ይድገሙ)
ዳግመኛም ሰውን ከምትወድ ከበጎነትህ እንለምንሃለን፤ ስለምንወዳቸው ስለ ወንዶቹና ስለ ሴቶቹ አገልጋዮችህ፣ ስለ አባቶቼ፣ ስለ ወንድሞቼና ስለ እህቶቼ፣ ስለ እኔም ስለ ደካማው አገልጋይህ በተቀደሰው መሠዊያህ ፊት ራሳቸውን ስላዘነበሉት ሰዎች እንለምንሃለን፤ የምሕረትህን መንገድ አዘጋጅልን፤ የኃጢአታችንን ማሰሪያ ሁሉ ቁረጥልን፤ አቤቱ አውቀን ወይም ሳናውቅ የሠራነውን፣ በሽንገላ ወይም በክፉ ልብ ቢሆን፤
Now again we pray and entreat of Thy goodness, O lover of man, on behalf of these Thy servants and handmaids, my fathers and my brothers and my sisters, and also on my own behalf, on me Thy feeble servant, and on behalf of them that bow their heads before Thy holy altar: prepare for us the way of Thy mercy, break and sever all the bonds of our sins, whether we have trespassed against Thee, O Lord, wittingly or unwittingly or in deceit or in evilness of heart,
መሂ በግብር እመሂ በነቢብ እስመ አንተ ታአምር ድካሞ ለሰብእ ኦ ኄር ወመፍቀሬ ሰብእ... (ይድገሙ)
በሥራም ሆነ በንግግር ወይም በሕሊና ማነስ የሠራነውን፤ አንተ የሰውን ድካም ታውቃለህና፤ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆንክ ቸሩና ሰውን የምትወድ አምላክ ሆይ፤ አቤቱ የኃጢአታችንን ስርየት ስጠን፤ ባርከን፣ ቀድሰን፣ ነጻም አውጣን፤ ሕዝብህንም ሁሉ ፍታቸው፤ በስምህ ፍርሃትም ሙሉን፤ ቅዱስ ፈቃድህንም በመሥራት አጽናን፤ ቸር መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ለአንተ ክብርና ጽናት ይገባል፤
whether in deed or in work or through smallness of understanding, for Thou knowest the feebleness of man. O good lover of man and Lord of all creation, grant us, O Lord, forgiveness of our sins, bless us and purify us and set us free and absolve all Thy people and fill us with the fear of Thy name, and establish us in the doing of Thy holy will. O Good, for Thou art our Lord and our God and our Savior Jesus Christ, to Thee we send glory and honor with Thy good
ስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ዘዕሩይ ምስሌከ... ይእዜኒ ወዘልፈኒ... ይኩኑ ፍቱሐነ እምአፈ ሥላሴ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ...
ከቸር ሰማያዊ አባትህና ሕይወትን ከሚሰጥ ካንተ ጋር በትክክል ከሚተካከል ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። በዚህች ዕለት የሚያገለግሉ አገልጋዮችህ ካህኑ፣ ዲያቆኑና ቀሳውስቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ እኔም ደካማው አገልጋይህ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በአንዲት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በአሥራ አምስቱ ነቢያት ስም፤
heavenly Father, and Holy Spirit, the life-giver, who is co-equal with Thee, both now and ever and world without end. Amen. May Thy servants who serve on this day, the priest and the deacon and the clergy and all the people, and I myself Thy poor servant, be absolved and set free and cleansed out of the mouth of the Holy Trinity, the Father and the Son and the Holy Spirit, and out of the mouth of the one holy apostolic church, and out of the mouths of the fifteen prophets, and out of the
እምአፈ ፲ወ፪ቱ ሐዋርያት ወእምአፈ ፸ወ፪ቱ አርድእት እለ አገልገሉ ወእምአፈ ነጋሬ መለኮት ማርቆስ ወንጌላዊ ሐዋርያ ወሰማዕት...
በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም፣ በሰባ ሁለቱ አርድእት ስም፣ መለኮትን በተናገረ በሐዋርያውና በሰማዕቱ በማርቆስ ወንጌላዊ ስም፤ ቸር መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ለአንተ ክብርና ጽናት ይገባል፤ ከቸር ሰማያዊ አባትህና ሕይወትን ከሚሰጥ ካንተ ጋር በትክክል ከሚተካከል ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
mouths of the twelve apostles, and out of the mouths of the seventy-two disciples the ministers, and out of the mouth of the speaker of divinity, the evangelist Mark the apostle and martyr: O Good, for Thou art our Lord and our God and our Savior Jesus Christ, to Thee we send glory and honor with thy good heavenly Father, and Holy Spirit, the life giver, who is co-equal with Thee, both now and ever and world without end. Amen.
ኩኑ ፍቱሐነ ወንጹሐነ እምአፈ ሥላሴ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወእምአፈ ፲ወ፭ቱ ነቢያት ወእምአፈ ፲ወ፪ቱ ሐዋርያት ወእምአፈ ፸ወ፪ቱ አርድእት...
በዚህች ዕለት የሚያገለግሉ አገልጋዮችህ ካህኑ፣ ዲያቆኑና ቀሳውስቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ እኔም ደካማው አገልጋይህ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በአንዲት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በአሥራ አምስቱ ነቢያት ስም፣ በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም፣ በሰባ ሁለቱ አርድእት ስም፣ መለኮትን በተናገረ በሐዋርያውና በሰማዕቱ በማርቆስ ወንጌላዊ ስም፤
May Thy servants who serve on this day, the priest and the deacon and the clergy and all the people, and I myself thy poor servant, be absolved and set free and cleansed out of the mouth of the holy Trinity, the Father and the Son and the Holy Spirit, and out of the mouth of the one holy apostolic church, and out of the mouths of the fifteen prophets, and out of the mouths of the twelve apostles, and out of the mouths of the seventy-two disciples the ministers, and out of the mouth of the
እምአፈ ማርቆስ ወንጌላዊ ሐዋርያ ወሰማዕት ወእምአፈ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ወቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወቅዱስ አትናቴዎስ ወቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወቅዱስ ቄርሎስ ወቅዱስ ጎርጎርዮስ ወቅዱስ ባስልዮስ ወእምአፈ ፫፻፲፰ቱ ጻድቃን እለ ተጋብኡ በኒቅያ...
መለኮትን በተናገረ በሐዋርያውና በሰማዕቱ በማርቆስ ወንጌላዊ ስም፣ በከበሩት ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሳዊሮስ፣ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ በቅዱስ አትናቴዎስ፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በቅዱስ ቄርሎስ፣ በቅዱስ ጎርጎርዮስና በቅዱስ ባስልዮስ ስም፤ አርዮስን ለማውገዝ በኒቂያ በተሰበሰቡት በ፫፻፲፰ቱ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ስም፤ መቅዶንዮስን ለማውገዝ በቁስጥንጥንያ በተሰበሰቡት በ፩፻፵ቱ ሊቃውንት ስም፤
speaker of divinity, the evangelist Mark the apostle and martyr: and out of the mouths of the honored Patriarchs St. Severus and St. Dioscorus and St. Athanasius and St. John Chrysostom and St. Cyril and St. Gregory and St. Basil: and out of the mouths of the 318 orthodox that assembled in Nicaea to condemn Arius, and out of the mouths of the 150 that assembled in Constantinople to condemn Macedonius,
እምአፈ ፪፻ቱ እለ ተጋብኡ በኤፌሶን በእንተ ንስጥሮስ ወእምአፈ ሊቀ ጳጳሳትነ... ወእምአፈ ድንግል እመቤታችን ቅድስት ማርያም... ስምከ ቅዱስ ወቡሩክ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ...
ንስጥሮስን ለማውገዝ በኤፌሶን በተሰበሰቡት በ፪፻ቱ ሊቃውንት ስም፤ በከበረው በሊቀ ጳጳሳችንና በብፁዕ ጳጳሳችን ስም፤ እኔም ኃጢአተኛውና ደካማው በምሆን በኔ በአገልጋይህ ስም፤ የተፈቱና የነጹ ይሁኑ፤ ድንግል በምትሆን በእመቤታችን በቅድስት ማርያም ስም፤ ቅዱስ ስምህ የተባረከና የከበረ ነውና፤ ቅዱስ ሥላሴ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
and out of the mouth of the 200 that assembled in Ephesus to condemn Nestor, and out of the mouth of the honored Patriarch and the blessed Archbishop, and out of the mouth of me also the sinful and miserable and poor, O may they be absolved and set free, and out of the mouth of our Lady Holy Mary, of twofold virginity, mother of God, the new loom; for Thy holy name is blessed and full of glory, O holy Trinity, Father and Son and Holy Spirit, both now and ever and world without end. Amen.
እንተ ሰላም ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር በምሕረቱ ሰላመ ይጸግወነ
እግዚአብሔር በቸርነቱ ሰላምን ይሰጠን ዘንድ ስለ ሰላም እንለምናለን
For the peace holy things we beseech, that God may grant us peace through His Mercy
እንተ ሃይማኖት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር በንጽሕና ይዕቀብ ሃይማኖተነ። በእንተ አሐቲ ቅድስት ጉባኤ ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር ይዕቀበነ እስከ ፍጻሜነ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ።
እግዚአብሔር እምነታችንን በንጽሕና ይጠብቅልን ዘንድ ስለ ሃይማኖታችን እንለምናለን። እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አንድነት እስከ ፍጻሜያችን ድረስ ይጠብቀን ዘንድ ስለ አንድነታችን እንለምናለን።
For our Faith we beseech, that God may grant us to keep the faith in purity. For our congregation we beseech, that God may keep us unto the end in the communion of the Holy Spirit.
