ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
አኵቶ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናያት ላዕሌነ መሐሪ አቡሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ ሰወረነ ወረድአነ ወዐቀበነ ወአቅረበነ ኀቤሁ ወተወክፈነ ኀቤሁ ወአጽንዐነ ወአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት።
መልካም ነገርን ለሚያደርግልን ለምሕረት አምላክ ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት ምስጋና እናቀርባለን፤ ሰውሮናልና፣ ረድቶናልና፣ ጠብቆናልና፣ ወደ እርሱ አቅርቦናልና፣ ጥበቃውንም አብዝቶልናልና፣ አበርቶናልና፣ እስከዚችም ሰዓት አድርሶናልና።
We give thanks unto the doer of good things unto us, the merciful God, the Father of our Lord and our God and our Savior Jesus Christ: for He hath covered us and succored us, He hath kept us and brought us nigh and received us unto Himself, and undertaken our defense, and strengthened us, and brought us unto this hour.
ሥአል እንከ ወናስተበቊዕ እምነ ኂሩቱ ከመ ይዕቀበነ እግዚአብሔር አምላክነ በዛቲ ዕለት ቅድስት ወበኵሉ መዋዕለ ሕይወትነ በኵሉ ሰላም። ዲያቆን፦ ጸልዩ።
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር አምላካችን በዚህች በተቀደሰች ዕለትና በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በፍጹም ሰላም ይጠብቀን ዘንድ እንለምነው። ዲያቆን፦ ጸልዩ።
Let us therefore pray unto Him that the Almighty Lord our God keep us in this holy day and all the days of our life in all peace. Deacon: Pray ye.
ግዚእ እግዚአብሔር አኃዜ ኵሉ አቡሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነአኵተከ ዲበ ኵሉ ወበእንተ ኵሉ ወውስተ ኵሉ እስመ ሰወርከነ ወረዳእከነ ወዐቀብከነ ወአቅረብከነ ኀቤከ ወተወከፍከነ ወአጽናዕከነ ወአብጻሕከነ እስከ ዛቲ ሰዓት።
ጌታ አምላካችን ሁሉን የምትገዛ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፤ ስለ ሁሉ ነገር፣ በሁሉ ነገር ውስጥ፣ በሁሉ ነገር ላይ እናመሰግንሃለን፤ ሰውረኸናልና፣ ረድተኸናልና፣ ጠብቀኸናልና፣ ወደ አንተ አቅርበኸናልና፣ ተቀብለኸናልና፣ ጠብቀኸናልና፣ አበርትተኸናልና፣ እስከዚችም ሰዓት አድርሰኸናልና።
Master, Lord God Almighty, the Father of our Lord and our God and our Savior Jesus Christ, we render Thee thanks upon everything, for everything and in everything, for Thou hast covered us and succored us, hast kept us and brought us nigh, and received us unto Thyself, and undertaken our defense, and strengthened us and brought us unto this hour.
ሡ ወአስተብቊዑ ከመ ይምሐረነ እግዚአብሔር ወይሣሃል ላዕሌነ ወይቀበል ጸሎተ ወአስተብቊዖተ እምነ ቅዱሳኑ በእንቲአነ ዘኵሎ ጊዜ ከመ ይረስየነ ድልዋነ ለተወክፎ ምሥጢር
እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ በእኛም ላይ ይቅር ይል ዘንድ አቤቱ ይቅር በለን እያልን እንለምነው
Entreat ye and beseech that the Lord have pity upon us and be merciful to us
ርያላይሶን። ተንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ኪርያላይሶን። ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Kyrie eleison. Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
ካዕበ ናስተበቊዕ ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ ውስተ ቅድስት አሐቲ እምቅዱሳት ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ በኵራተ አሥራተ አኰቴተ ዝክረ ዘብዙኅ ወዘውኅድ በኅቡዕ ወበግሃድ ወበእንተ እለኒ ይፈቅዱ ያብኡ ወአልቦሙ ከመ ይጸግዎሙ ፍቅደ ልቦሙ ዘሰማያዊት መንግሥት ይጸግዎሙ ኵሎ ኃይለ በረከት...
ደግመን ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርን በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መባ፣ መሥዋዕት፣ በኵራት፣ አሥራት፣ የምስጋና መባ፣ መታሰቢያ የሚሆን በምሥጢርም ሆነ በግልጽ፣ ጥቂትም ሆነ ብዙ ለሚያቀርቡ ሰዎች የአምላካችንን ዝግጁ ልቡናቸውን ይቀበል ዘንድ፣ የሰማያዊውን መንግሥት ይሰጣቸው ዘንድ እንለምነው፤ የባረከው ሁሉ ኃይል ለአምላካችን ይገባል።
And again let us beseech the Almighty Lord, the Father of the Lord our Savior Jesus Christ, on behalf of those who bring an oblation within the one holy universal church, a sacrifice, first-fruits, tithes, a thank offering, a memorial, whether much or little, in secret or openly, and of those who wish to give and have not wherewith to give, that He accept their ready mind, that He vouchsafe to them the heavenly kingdom; power over all works of blessing belongs to the Lord our God.
ልዩ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ
መባ ስለሚያገቡ ሰዎች ጸልዩ
Pray for them who bring an oblation.
ወከፍ መባኦሙ ለአኃው ወተወከፍ መባኦን ለአኃት ወለነኒ ተወከፍ መባአነ ወቊርባነነ
የወንዶችን መባ ተቀበል የሴቶችን መባ ተቀበል የኛንም መባችንን ቁርባናችንን ተቀበልልን
Accept the oblation of our brethren, accept the oblation of our sisters, and ours also accept, our oblation and our offering.
ግዚእ አምላክነ ዘኵሎ ትእኅዝ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ ውስተ ቅድስት አሐቲ እምቅዱሳት ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ በኵራተ አሥራተ አኰቴተ ዝክረ ዘብዙኅ ወዘውኅድ በኅቡዕ ወበግሃድ ወበእንተ እለኒ ይፈቅዱ ያብኡ ወአልቦሙ
ሁሉን የምትገዛ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መባ፣ መሥዋዕት፣ በኵራት፣ አሥራት፣ የምስጋና መባ፣ መታሰቢያ የሚሆን በምሥጢርም ሆነ በግልጽ፣ ጥቂትም ሆነ ብዙ ለሚያቀርቡ ሰዎችና መስጠት እያሻቸው ምንም ለሌላቸው ሰዎች እንለምንሃለን።
Lord our God who art Almighty, we pray Thee and beseech Thee for them that bring an oblation within the one holy universal church, a sacrifice, first-fruits, tithes, a thank offering, a memorial, whether much or little, in secret or openly, and for those who wish to give and have not wherewith to give.
ወክፎተ ልቦሙ ጸግው ለኵሎሙ ወዕሴተ በረከትከ ግበር ሎሙ ውስተ ኵሎሙ በዝንቱ ወልድከ ዋሕድ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
የእያንዳንዳቸውን ዝግጁ ልቡናቸውን ተቀበል፤ የበረከትህንም ዋጋ ለሁሉም ክፈላቸው፤ በአንድ ልጅህ በእሱ በኩል ለአንተ ክብርና ጽናት ይገባል፤ ከእሱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Thy acceptance of their ready mind grant Thou unto every one: let the recompense of blessing be a portion to all of them: through Thy only begotten Son, through whom to Thee with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion, both now and ever and world without end. Amen.
ንሥኡ ለጸሎት። እግዚኦ ተሣሃለነ።
ለጸሎት ተነሡ። አቤቱ ይቅር በለን
Stand up for prayer. Lord have mercy upon us.
ላም ለኵልክሙ። ምስለ መንፈስከ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ከመንፈስህ ጋር
Peace be unto you all. And with Thy spirit.
እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቢጸ ምስለ አብ ቀዳማዊ ቃል ንጹሕ ቃለ አብ ወቃለ መንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ አንተ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት ወአቅደምከ ነጊረ ከመ ትከውን በግዐ ዘአልቦ ነውር በእንተ ሕይወተ ዓለም
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ከቀዳማዊ አብ ጋር አንድ የምትሆን፣ ንጹሕ የምትሆን የአብ ቃል፤ ሕይወትን የምትሰጥ የመንፈስ ቅዱስም ቃል፤ ከሰማያት የወረድህ የሕይወት እንጀራ አንተ ነህ፤ ስለ ዓለሙ ሁሉ መዳን ነውር የሌለበት በግ መሥዋዕት እንድትሆን አስቀድመህ ተናግረሃል።
O my Master, Jesus Christ, co-eternal pure Word of the Father, and Word of the Holy Spirit, the life giver, Thou art the bread of life which didst come down from heaven, and didst foretell that Thou wouldest be the Lamb without Spot for the life of the world:
ይእዜኒ ንስእል ወናስተበቊዕ እምነ ኂሩትከ ሠናይት ኦ መፍቀሬ ሰብእ አርኢ ገጸከ ላዕለ ዝንቱ ኅብስት ወዲበ ዝንቱ ጽዋዕ ዘአንበርነ ዲበ ዝንቱ ታቦት መንፈሳዊ ዘአንተ አምበርከ ባርኮ ለዝንቱ ኅብስት ወቀድሶ ለዝንቱ ጽዋዕ ወአንጽሖሙ ለክልኤሆሙ።
አሁንም ሰውን ከምትወድ ከበጎነትህ ቸርነት እንለምንሃለን፤ በዚህ በመንፈሳዊ ታቦትህ ላይ ባስቀመጥነው በዚህ እንጀራ ላይና በዚህ ጽዋ ላይ ፊትህን አብራ፤ ይህን እንጀራ ባርከው፤ ይህንም ጽዋ ቀድሰው፤ ሁለቱንም አንጻቸው።
We now pray and beseech of Thine excellent goodness, O lover of man, make Thy face to shine upon this bread, and upon this cup, which we have set upon this spiritual ark of Thine: Bless this bread, and hallow this cup, and cleanse them both.
